የሕግ እና ተቋማዊ ማሻሻያዎች
መጋቢት 2010 እንደሀገር በመጣው ለውጥ ምክንያት ሰፊ የማሻሻያ ስራዎች የተሰራበት እና አመርቂ ውጤቶች የተገኙበት ጉዳይ በሕግ እና በተቋማት ላይ የተደረጉ የማሻሻያ ስራዎች ናቸው። እነኚህ የማሻሻያ ስራዎች ከለውጡ በፊት በኢትዮጵያ የነበረው የዴሞክራሲ ጉድለትን፣ የሰብዓዊ መብቶች አለመከበርን፣ የዳኝነት እና የፍትሕ ተቋማት ነጻ እና ገለልተኛ ሆኖ በማገልገል ረገድ የነበረ ውስንነትን እንዲሁም የመንግስት አሰራር ግልጽነት እና ተጠያቂነት መጓደልን በማረም ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽዖ አበርክተዋል።
የሕግ ማሻሻያ ስራዎቹ የተሰሩት የለውጡ መንግስት ኃላፊነቱን እንደተቀበለ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ምሁራን እና በሕብረተሰቡ ዘንድ በገለልተኝነታቸው እና በሙያ ብቃታቸው ተቀባይነት ካላቸው ዜጎችን አባል አድርጎ በፍትሕ ሚኒስቴር ስር በተቋቋመው የሕግ እና ፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ምክር ቤት አማካኝነት ነው።

በዚህም መሰረት፡–
- ቀደም ሲል በዜጎች የሰብዓዊ መብቶች ላይ ከፍተኛ ገደብ ጥለው የነበሩ እና ለመጠነ ሰፊ የዜጎች የሰብዓዊ መብት ጥሰት አስተዋጽዖ የነበራቸውን ሕጎች ማለትም፡
- የጸረ–ሽብር አዋጅ፣
- የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ
- የሚዲያ ሕግ
በማሻሻል፤
- ቀደም ሲል ዴሞክራሲን እና የመንግሰት አሰራር ግልጽነትን እና ተጠያቂነትን በማረጋገጥ ረገድ ክፍተት የነበራቸውን ተቋማት የሚያሻሽሉ ሕጎችን እና ይህንን ሊያረጋገጡ አዳዲስ ሕጎችን ማለትም፡
- የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ
- የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አዋጅ
- የአስተዳደር ሥነ–ሥርዓት አዋጅን
በማዘጋጀት፤
- የዜጎችን ደሕንነት እና ሰብዓዊ መብት እንዲሁም የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚረዱ ሕጎችን ማለትም፡
- የጦር መሣሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ
- በሰው የመነገድ እና ሰውን በሕገ–ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅን
በማዘጋጀት፤
- የኢትዮጵያን የሕግ እና የፍትሕ ዘርፍ ዘመኑ ከደረሰበት የእድገት ደረጃ ጋር አብሮ ለማስኬድ የሚያስችሉ የሕግ ስርዓት ማሻሻያዎችን የሚያመጡ ሕጎችን ማለትም፡
- የወንጀል ሥነ–ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ መድብል
- የንግድ ሕግ መድብል
- የግልግል ዳኝነት እና የእርቅ አሰራር ስርዓት አዋጅን
በማዘጋጀት እና በማጸደቅ በሕግ እና ፍትሕ ዘርፉ ላይ ከፍተኛ አዎንታዊ ለውጥን ለማምጣት ተችሏል።
በሌላ በኩል የፍርድ ቤቶችንነጻነት እና ገለልተኝነት የሚያረጋግጡ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ እና የፌዴራል ዳኝነት አስተዳደር አዋጅ ጸድቀው በስራ ላይ እንዲውሉ በማድረግ የዳኝነትን ነጻነትን ይበልጥ ለማረጋገጥ ተችሏል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የፌዴራል ዐቃብያነ ሕግን ነጻነት እና ገለልተኝነት ለማረጋገጥ ያስቻለው የፌዴራል ዐቃብያነ ሕግ መተዳደሪያ ደንብም ጸድቆ ስራላ ይውሏል።
ከእነኚህ በተጨማሪ አዲስ የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነምግባር አዋጅን በማጸደቅ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ ከመጡት ተቋማዊ ማሻሻያዎች ጋር በማስተሳሰር ለመጀመሪያ ጊዜ ነጻ፣ ተዓማኒ እና ፍትሐዊ ብሔራዊ ምርጫን ለማካሔድ ተችሏል። በተያያዘም ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን ይበልጥ ለማጠናከር እንዲቻል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ እና የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ማቋቋሚያ አዋጅ ተሻሽለው እንዲጸድቁ እና ስራ ላይ እንዲውሉ በማደረግ ተቋማቶቹ ለዜጎች ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችላቸውን ቁመና እንዲላበሱ ለማድረግ ተችሏል።