የሽግግር ፍትሕ በኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች የተፈጠሩ የፍትሕ መጓደሎችን እና መሰረታዊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በመመርመር አጥፊዎችን በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ፣ ተጎጂዎች መልሰው የሚቋቋሙበት እና ካሳ የሚያገኙበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እንዲሁም በአጠቃላይ በሀገራችን የተለያዩ የታሪክ ምዕራፎች የተፈጸሙ በደሎችን አስመልክቶ እውነትን በማፈላለግ በእውነት እና በይቅርታ ላይ የተመሰረተ እርቅን በማምጣት ሀገራችንን ከሚፈታተናት የግጭት አዙሪት ለማውጣት ይቻል ዘንድ የኢትዮጵያ ፌዴራልዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት በጥቅምት ወር 2015 ዓ.ም የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ዝግጅትን በይፋ አስጀምሯል።

የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ዝግጅቱ ገለልተኛ በሆኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን፣ የሕግ ባለሙያዎችን እና በተለይም በሽግግር ፍትሕ ረገድ ልዩ የከፍተኛ ትምህርት ዝግጅት ባላቸው ባለሙያዎች አማካንነት በፍትሕ ሚኒስቴር አስተባባሪነት ተዘጋጅቷል። ረቂቅ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ሰነዱ ላይ በመላ ሀገሪቱ 80 ሕዝባዊ መድረኮች ተዘጋጅተው ውይይት የተደረገበት ሲሆን በእነኚህ መድረኮች ላይ 4800 የሚሆኑየህብረተሰበተወካዮች፣ተጎጂዎች፣የመንግስትየስራኃላፊዎች፣የሲቪልማህበረሰብተወካዮች፣በሽግግርፍትሕዙሪያአለምአቀፍኤክሰፐርቶችእናየዲፕሎማቲክማህበረሰብተሳትፈውባቸዋል።
በዚህ አሳታፊ ሂደት ያለፈው የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ዝግጅት ከተደረጉት መድረኮች በተገኙ ግብዓቶች ዳብሮ ሚያዚያ 8 ቀን 2016 ዓ.ም በኢ.ፌ.ዲ.ሪየሚኒስትሮችምክርቤትጸድቋል።
የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲው በውስጡ፡-
- የወንጀል ተጠያቂነትን፣
- እውነት የማፈላለግን፣ ይፋ የማውጣትን እና የዕርቅ ተግባርን፣
- በቅድመ–ሁኔታ ላይ ሰለሚመሰረት ምህረት፣
- የማካካሻ ስርዓትን እና
- ተቋመዊማሻሻያን
የሚመለከቱ ዝርዝር አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።
እነኚህንም አቅጣጫዎች በመከተል ፖሊሲውን ለማስፈጸም የሚረዱ ሕጎችን የማርቀቅ ስራ በመከናወን ላይ የሚገኝ ሲሆን እነኚህም፡
- የልዩ ዐቃቤ ሕግ ጽ/ቤትን፣ የእውነት ኮሚሽንን እና የማጥራት ኮሚሽንን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ በመድብል
- የዓለም አቀፍ ወንጀሎች ረቂቅ አዋጅ እና
- የልዩ ችሎት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ናቸው።
የእነኚህን ሕጎች ረቂቅ የማዘጋጀት ስራው ፖሊሲውን ባዘጋጀው ገለልተኛ የባለሙያዎች የስራ ቡድን የተከናወነ ሲሆን የረቂቅ ሕጎቹ ዝግጅት ሲጠናቀቅ ፖሊሲው በጸደቀበት የአካሄድ አግባብ ሰፊ በሆነ ሕዝባዊ ምክክር እንዲያልፍ በማድረግ ከምክክሩ የሚገኙ ገንቢ ግብዓቶች እንዲካተቱበት የሚደረግ ይሆናል።