የሕግ ተፈጻሚነት ክትትሉ የሚያተኩረው በመላው አገሪቷ ተፈጻሚ የሆኑ እንዲሁም በፌደራል ተቋማት ብቻ የሚተገበሩ የፌደራል ሕጎች ለወጡለት ዓላማ በወጥነት እየተተገበሩ መሆኑን በማረጋገጥ ላይ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ተቋማችን ሪፖርቶችን ያዘጋጃል፣ በመጀመሪያው ሪፖርት ላይ የተሰጡ ምክረ ሀሳቦች መተግበራቸውን ለማረጋገጥም የዳግም ክትትሎችን ያደርጋል፡፡