"ትናንት፣ ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና" በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀ ሰነድ ዙሪያ የፍትህ ሚኒስቴር አመራሮች ውይይት አካሄዱ

Ministry of Justice Leaders Discuss Document Prepared Under the Theme "Yesterday, Today and Tomorrow for Ethiopia's Sovereignty"

“ትናንት ዛሬና ነገ ለኢትዮጵያ ልዕልና” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀ “የመጋቢታውያን የለውጥ ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎች” ሰነድ ላይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በተገኙበት ውይይት ተካሂዷል።

ውይይቱን በንግግር የከፈቱት በፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ተስፋዬ ዳባ እንዳሉት ከመጋቢት እስከ መጋቢት በሚል በዛሬው እለት ለውይይት የቀረበው ሰነድ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም በኢትዮጵያ የፓለቲካ ታሪክ ቁልፍ የታሪክ መዝገብ የሚቀመጥ ታሪክ የተመዘገበበትና ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር የተደረገበት እለት መሆኑን አስታውሰዋል።

አያይዘውም በኢትዮጵያ የመንግሥት ለውጥ ሂደት ከተደረገ በኋላ የመጡ ለውጦች ምንድን ናቸው፣ ምን ተግዳሮቶች ገጠሙ የሚሉና የወደፊት ተስፋዎችስ ምንድን ናቸው የሚሉት መሠረታዊ የውይይት መነሻዎች እንደሆኑ አንስተዋል።

ቀጥሎም “ትናንት ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና” በሚል ለውይይት የተዘጋጀውን ሰነድ በፍትሕ ሚኒስቴር የመንግሥት ሕግና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ በላይሁን ይርጋ አቅርበዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው በገለጻቸው በሰላማዊ መንገድ የተካሄደው የመንግሥት ሽግግር ሰባተኛ ዓመት ሲታሰብ በመንግሥት የተገቡ ቃሎችን ተግባራዊ በማድረግ ባህል እያደረጉ መሄድ እንደሚገባ አውስተው በተለይም እንደ ፍትሕ ዘርፍ የተያዙ እቅዶችን በተመለከተ ያለበትን ደረጃ በመገምገምና የተገኘውን እድል በአግባቡ በመጠቀም በቀጣይ ወደተሻለ ለውጥ ለመጓዝ መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

አያይዘውም ባለፉት ሰባት አመታት የተመዘገቡ ፓለቲካዊ ለውጥ፣ ኢኮኖሚን የማሻሻል ለውጥ፣ የተቋማት ሪፎርም ለውጥ ሂደት፣ በዲፕሎማሲ ስራዎች ላይ የተመዘገበ ለውጥና የተገኙ ውጤቶችን አብራርተዋል።

በነዚህ ጊዚያቶች አዲስ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ለማለማመድ በተለይም የፓለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት የተሄደበት ርቀት ተጠቃሽ መሆኑን አንስተው ከፍትሕ ዘርፉ ጋር በተያያዘም የፍትሕ ሪፎርሙን ተከትሎ ብዙ የሕግ ማሻሻያዎች መደረጋቸውን፣ በከባድና በተደራጁ ወንጀል ምርመራ ስራዎችና በሌሎች ተግባራት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን አንሰተው የተሰሩ ስራዎች እንዳሉ ሆነው ባልተሰሩ ሌሎች ተግባራት ላይ ደግሞ ትኩረት በማድረግ በቀጣይ መሥራት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

ቀጥሎም ለውይይት መነሻነት በቀረበው ላይ ከተሳታፊዎች በተነሱት ሀሳብና አስተያየቶች ላይ ከመድረኩ ማጠቃለያ ተሰጥቶባቸው ውይይቱ ተጠናቋል።

Tagged Under: challenges change democratic reform Economic development Government Implementation Institutional Reform judicial judicial reform legal Legal Reform National National Security National Unity opportunities Policy Policy Implementation political political stability Political Transition progress reform reforms Rule of Law Security sovereignty transition
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች