የአንድ ዕቅድ አንድ ሪፖርት አሰራርን ተግባራዊ ማድረግ የክልል ፍትሕ ቢሮዎች እና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የቅንጅትና ትብብር ስራዎችን እንደሚያጠናክር ተመላከተ

Implementation of One Plan One Report System Expected to Strengthen Coordination and Collaboration Between Regional Justice Bureaus and the Ministry

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የክልል ጉዳዮች ክትትል እና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት አሰተባባሪነት የክልል ፍትሕ ቢሮዎች የ2017 በጀት ዓመት የ9ወራት የመደበኛ እና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈፃፀም ላይ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት በተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ የሚኒስትር ዴኤታ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መዝሙር ያሬድ እንደተናገሩት፣ መድረኩ የተዘረጋውን የአንድ እቅድ አንድ ሪፖርት እሰራርን መሠረት በማድረግ መዘጋጀቱን ጠቁመው፣ ይህንንም ሥርዓት ተግባራዊ ማድረግ በክልል ፍትሕ ቢሮዎች እና በፍትሕ ሚኒስቴር መካከል ያለውን የቅንጅት እና የትብብር ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል ያስችላል ብለዋል፡፡

አክለውም መድረኩ በዋናነት ዓላማ ያደረገው በተለይም የዕቅድ አመላካቾች የተናበቡ መሆናቸውን እንዲሁም ዕቅድና ሪፖርቶች በይዘት ደረጃ ምን መምሰል አለባቸው የሚለውን በመለየት ወጥ በሆነ መልኩ እንዲዘጋጁ ማድረግ እንዲቻል ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ ጉዳዩችን መለየት እንዲሁም ክልሎች እርስ በእርስ የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ በማስቻል የቅንጅትና ትብብር አንድ መድረክን መፍጠር እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

የውይይት መድረኩ በዛሬ ውሎው የአፋር፤ የሶማሌ፤የጋምቤላ እና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፍትሕ ቢሮዎችን ለዐ/ሕግ የቀረቡ የምርመራ መዝገብ ብዛት እና የማጥራ ምጣኔ ፤የክርክር መዛግብት ብዛት እና የመርታት ምጣኔ፤ በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን በተመለከተ፤የክልል ወንጀል ይግባኝ አፈፃፀም፤ በውክልና የሚሰሩ የፌደራል ወንጀል ጉዳዩች የፍ/ቤት ውሳኔን በተመለከተ፤ ከሰብዓዊ መብት ማክበርና ማስከበር፤ የሀብት ማስመለስ ክርክርና የተመለሰ የሀብት መጠንን በተመለከተ፤ የዐቃብያነ ሕግ አቅም ግንባታ እና ሌሎች የመደበኛ ዕቅድ አካል የሆኑ ስራዎች አፈፃፀም መቅረብ ችሏል፡፡

የቀረቡ የክልል ፍትሕ ቢሮዎች የ2017 በጀት ዓመት የ9ወራት የመደበኛ ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን መሠረት በማድረግ በፍትሕ ሚኒስቴር ስትራቴጂክ ጉዳዩች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ መንግስቴ አማካኝነት ግብረመልስ ተሰጥቷል፡፡

በቀጣይም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ፤ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፤ የሲዳማ፤ የአማራ እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትሕ ቢሮ የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፤ በዕቅድ ትግበራው ወቅት የታዩ ክፍተቶች በፍትሕ ሚኒስቴር የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኖህ ታከለ አማካኝነት ተነስተው በቀጣይ ሊወሰዱ ስለሚገቡ የመፍትሔ እርምጃዎች ላይ አቅጣጫ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

በመጨረሻም በፍትሕ ሚኒስቴር የክልል ጉዳዮች ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አበራ አሰፋ አማካኝነት የክልል ፍትሕ ቢሮዎች የሪፖርት አቀራረብ ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን አሰመልክቶ አሰተያየት የተሰጠባቸው ሲሆን፤ የአንድ ዕቅድ አንድ ሪፖርት ሥርዓትን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ በቀጣይ ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን አመላክተዋል፡፡

መድረኩ ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን በቀጣይም የሪፖርት ማጠቃለያ ውይይትን ጨምሮ የፌደራል የወንጀል ጉዳዮች የስረ-ነገር ሥልጣንን እና የሽግግር ፍትሕ ፓሊስ ትግበራ ሂደትን በተመለከተ በፍትሕ ሚኒስቴር አማካኝነት ሰነዶች ቀርበው ሰፋ ያለ ውይይት እንደሚደረግ ተጠቁሟል፡፡

መድረኩንም የፍትሕ ሚኒስቴር የወንጀል ፍትሕ ስርዕትን ለማሻሻል ከአውሮፓ ህብረት በተደረገ ድጋፍ አዘጋጅቶታ፡፡

Tagged Under: budget year bureaus Capacity Building civil liberties Collaboration Coordination criminal data analysis federal fundamental rights Human Rights Implementation Justice Justice Ministry Legal Reform ministry monitoring one performance Performance Evaluation performance monitoring plan Regional Regional Justice Bureaus report report submission Strategic Planning transformation plan
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች