በአዋጅ ቁጥር 943/2008 ዓ.ም አንቀፅ 6(6) መሰረት፣ የፌደራል ሕጎች በአግባቡ መተግበራቸውን እና ወጥ የሆነ አተገባበር መኖሩን ማረጋገጥ እንዲሁም አስፈፃሚ የፌደራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሥራዎቻቸውን በሕግ መሰረት እየሰሩ መሆኑን መከታተል ከፍትሕ ሚኒስቴር ዋና ኃላፊነቶች መካከል አንዱ ነው፡፡ ይህንን ተልዕኮ መሰረት በማድረግ፣ ተቋማችን የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ጨምሮ የፌደራል ሕጎች አፈፃፀም እና የመንግሠት ተቋማት የሕግ ተገዢነት ላይ የክትትል ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡