ተቋማችን የመንግስት ተቋማትን የሕግ ተገዢነት ክትትል የሚያደርግ ሲሆን፣ የመንግሥት ተቋማት ለአስተዳደር ሕጎች ያላቸውን የሕግ ተገዢነት በተለይም ለፌዴራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ያላቸውን ተገዢነት ትኩረት ሰጥቶ በቅርበት ይከታተላል፡፡ በዚህም መሰረት ሪፖርቶችን ያወጣል፣ በተጨማሪም የሪፖርቶቹ ምክረ ሀሳቦች መተግበራቸውን ለማረጋገጥ የዳግም ክትትሎችን ያከናውናል፡፡