ታሪክ እና ዐበይት ክንውኖች

1900 ዓ.ም

በ1900 ዓ.ም የዳኝነት ስራ በመደበኛነት በፍርድ ቤት መሰራት ከመጀመሩ በፊትና በአገሪቱ አራት ዋና ዋና የስራ መሪዎች በነበሩ ጊዜ የዳኝነት ጉዳይ የሚመለከታቸው አፈ-ንጉሱን ነበር፡፡ የግዛት ክልል ገዢዎችም የዳኝነት ስራን በሰብሳቢነት ያከናውኑ ነበር፤ ጥቅምት 15 ቀን 1900 ዓ.ም. ከተሾሙ 11 የመጀመሪያ ሚኒስትሮች መካከል የፍርድ ሚኒስትር ይገኙበት ነበር። በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የፍርድ ሚኒስትር አፈ ንጉሥ ነሲቡ መስቀሉ ይባላሉ፡፡ በወንጀል እና በፍትሐ ብሔር ጉዳዮች የሚኒስትሩ የይግባኝ ሰሚነት ስራ የሚመራው “የፍትሐ ነገስት”ን መሰረት በማድረግ ነበር፡፡ ጥቅምት 15 ቀን 1900 ዓ.ም የፍርድ ሚኒስትሩ ከተሾሙ በኋላ ስራው ለአንድሚኒስትር ስለሚበዛ በሚል አጋዥ 12 ወንበሮች እና 6 ችሎቶች ተጨምረው ነበር።

1910 ዓ.ም

መጋቢት 14 ቀን 1910 ዓ.ም ህዝቡ በጃንሜዳ ተሰብስቦ ሚኒስትሮች ይነሱ የሚል ጥያቄ መሰረት መጋቢት 16 ቀን 1910 ዓ.ም ከጦር ሚኒስትሩ በስተቀር ሌሎች ሚኒስትሮች ሲሻሩ በጊዜው የፍርድ ሚኒስትር የነበሩት አፈንጉሥ ጥላሁን ከስልጣን እንዲነሱ ተደርጓል፡፡ በዚህም ምክኒያት በሚኒስቴር ደረጃ ይከናወን የነበረው የፍትህ አሰተዳደር ሥራ ሊቋረጥ ችሏል፡፡

1922 ዓ.ም

- በ1922 ዓ.ም የሚኒስትር መስርያ ቤቶች እንደገና እንዲቋቋሙ ተደረገ፡፡ የፍርድ ሚኒስትርም በድጋሚ ስራ ጀመረ፡፡
- በኢትዮጵያዊ እና በውጭ አገር ዜጎች መካከል የሚነሳን ክርክር በሚመለከት ይግባኝ ሰሚው ችሎት ንጉሱ ተሰይመውበት ዳኝነቱ እንዲካሄድ ተደርጎ ነበር፡፡

1923 ዓ.ም
ታህሳስ 2/1923 ዓ.ም የምህረት አዋጁን የማስፈጸም ተግባር ለፍርድ ሚኒስትር ተሰጠ።
1933 ዓ.ም
ንጉሱ ወደ ውጭ ሀገር በስደት ከሄዱበት ጊዜ አንስቶ እስከ 1933 ዓ.ም. የውጭ ወረራ ስለነበር ሀገሪቱ መንግስትም፤ የፍርድ ሚኒስትርም አልነበራትም፡፡
1934 ዓ.ም
ንጉሱ ከስደት ከተመለሱ በኋላ በ1934 ዓ.ም በአዋጅ ቁጥር 1/1934 መሰረት ነጋሪት ጋዜጣ ተቋቋመ፡፡
1935 ዓ.ም
1935 የዐቃብያነ ህግ አዋጅ ወጣ፤ ዐቃቤ ህግን በበላይነት የሚመራው የፍርድ ሚኒስቴር መስርያ ቤት ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በወንጀል ጉዳይ መንግስትን ወክሎ መከራከር የሚያስችል ስልጣን ተሰጠው፡፡
1938 ዓ.ም
በ1938 ዓ.ም ሁለት የውጭ ሀገር ተወላጆች በጠቅላይ ዐቃቤ ህግነትና በረዳት ጠቅላይ ዐቃቤ ህግነት ተሹመው ሰርተዋል፡፡ በዚህ ወቅት ተቋሙን በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግነት ከመሩት መካከል እስራኤላዊ ዜግነት ያላቸው ሚስተር ናታን ማሪን ይገኙበታል፡፡
1943 ዓ.ም
በ1943 ዓ.ም የወንጀል ምርመራ እና ከሶ የማስቀጣት ስራን የሚመራው ባለስልጣን መጠሪያ ከዋና ዐቃቤ ህግነት ወደ “ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ” ተብሎ እንዲቀየር ተወሰነ፡፡
1945 ዓ.ም
በ1945 ዓ.ም የፍርድ ሚኒስቴሩ ማዕከላዊ መንግስቱን የፍትህ አስተዳደር የመቆጣጠር ስልጣን ተሰጥቶታል
1948 ዓ.ም
1948 ዓ.ም ፍርድ ሚኒስትሩ መንግስትን ከማማከር ስራው በተጨማሪ በፓርላማው ጥሪ ሲደረግለት ቀርቦ በተነሱ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ያቀርብ ነበር፡፡
1954 ዓ.ም
በ1954 ዓ.ም የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ወጣ ፡፡ የፍርድ ሚኒስቴር ህጉን የሚያስፈፀምበትን ሥርዓት የሚደነግግ ከመሆኑም በላይ ፍርድ ቤቶች በወንጀል ጉዳይ ረገድ የሚኖራቸውን የፍሬ ነገር ስልጣን በተመለከተ ማሻሻያ ደንቦች ለማውጣት ሥልጣን ተሰጥቶት ነበር፡፡
1965 ዓ.ም
በ1965 ዓ.ም የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የተቋቋመ ሲሆን የጉባኤው ሰብሳቢ የፍርድ ሚኒስትር ነበሩ፡፡
1969 ዓ.ም
1969 ዓ.ም የተቋሙ ስም “የፍርድ ሚኒስቴር” መባሉ ቀርቶ “የህግና ፍትህ ሚኒስቴር” እንዲባል ተወሰነ፡፡
1975 ዓ.ም
በ1975 ዓ.ም የ1950ዎቹን ኮዶች ማሻሻልን ግቡ ያደረገ የኮዲፊኬሽን ስራ በይፋ ተጀመረ፡፡ በዚህ የኮዲፊኬሽን ስራ የወንጀል እና የፍትህብሄር ህጎችን ከነ ሥነ-ሥርዓት ህጎቻቸው፣ የንግድ ህግን እና ሌሎች በመድብል ደረጃ ሊወጡ የሚገቡ ህጎችን የሚያረቁ ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች የሚሳተፉባቸው ቡድኖች ተቋቁመው ነበር፡፡
1980 ዓ.ም
1980 ዓ.ም በኢህዲሪ ህገ-መንግስት መሰረት የፍትህ አሰተዳደርን በሃላፊነት የሚመራው አካል የፍትህ ሚኒስቴር ተብሎ እንደገና ተቋቋመ፡፡ የዐቃቤ ህግ መስሪያ ቤት ራሱን የቻለ የመንግስት አካል ሆኖ በመቋቋም በወንጀል እና በፍትሐብሔር ጉዳይ ከፍተኛ ሃላፊነት ተሰጥቶት ነበር፡፡
1984 ዓ.ም
ነሃሴ 11 ቀን 1984 ዓ.ም የኢፌዲሪ ልዩ ዐቃቤ ሕግ ጽ/ቤት በአዋጅ ቁጥር 22/1984 መሰረት ተቋቋመ፡፡ ህዳር 18 ቀን 1988 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ክሱን ለፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቀረበ፡፡
1985 ዓ.ም
በ1985 ዓ.ም የሽግግር መንግስቱ ማዕከላዊ ዐቃቤ ሕግ የተቋቋመ ሲሆን፤በአዋጅ ቁጥር 22/1985 መሰረት ተጠሪነቱ በቀጥታ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሆነ ልዩ ዐ/ህግ ፅህፈት ቤት ተቋቋሞ ነበር፡፡
1987 ዓ.ም
ፍትሕ ሚኒስቴር እና ማዕከላዊ ዐቃቤ ሕግ ተብለው የሚጠሩት ሁለት ተቋማት በአዋጅ ቁጥር 4/1987 መሰረት ተቀላቀሉ፡፡ በ1988 ዓ.ም ከየነበሩበት ህንጻ ለቀው አሁን ፍትሕ ሚኒስቴር ዋናው መስሪያ ቤት ወደሚገኝበት ህንጻ መጥተው መቀላቀል ቻሉ፡፡
2001 ዓ.ም
2001 የመሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ (ቢፒአር) ተተገበረ፡፡
2003 ዓ.ም
በ2003 ዓ.ም የወንጀል ፍትሕ ፖሊሲ ጸድቆ ወደ ስራ ገባ
2008 ዓ.ም
በ2008 ዓ.ም በአዋጅ ቁጥር 916/2008 አንቀጽ 16 (14) እና (15) በወንጀል ጉዳዮች የዓለም አቀፍ ትብብርን በሚመለከት የሚከናወኑ ሥራዎችን እንዲያስተባብር እንዲሁም ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸውን አለም ዓቀፍና አህጉራዊ የሰብአዊ መብት ስምምነቶች አፈፃፀማቸውን እንዲከታተል፤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመመካከር ለሚነሱ ጉዳዮች አግባብ ያለው ምላሽ እንዲሰጥ፤ የስምምነቶቹን ብሔራዊ የአፈፃፀም ሪፖርት እንዲያዘጋጅ ስልጣን ተሰጠው፡፡
2008 ዓ.ም
ተቋሙ በአዋጅ ቁጥር 943/2008 መሰረት በገቢዎች እና ጉምሩክ፣ በጸረ ሙስና ኮሚሽን እና ሸማቾች ዐቃቤያነ ህግ ሲመሩ የነበሩ የዐቃቤ ህግነት ስራዎችን በመጠቅለል መጠሪያው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ሆኖ በአዲስ መልክ ተቋቁሞ የነበረው ሚያዚያ 24 ቀን 2008 ዓ.ም ነበር፡፡
2009 ዓ.ም
በ2009 ዓ.ም. ለክልል ፍትሕ ቢሮዎች ተሰጥቶ የነበረው ውክልና ተነስቶ ፍትሕ ሚኒስቴር (በወቅቱ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ) ቀጥሮ በመደባቸው ዐቃቤያነ ሕግ በክልሎች የሚፈጸሙ የፌዴራል መንግስት ስልጣን ስር የሚወድቁ የወንጀል ጉዳዮችን እንዲከታተሉ ተደረገ፡፡ ሆኖም በ2010 ዓ•ም አደረጃጀቱ ታጥፎ፤ የተነሳው ውክልና ተመልሶ ለክልል ፍትሕ ቢሮዎች ተሰጠ፡፡
2010 ዓ.ም.
ከ2010- 2012 ዓ.ም የሕግ እና ፍትሕ ሪፎርም ስራዎች በትኩረት ተከናውነዋል፡፡ በተለይም መሰረታዊ ችግር ያሉባቸውን ሕጎች ለይቶ የማሻሻል ስራው ለብዙ ሕጎች መውጣት እና መሻሻል ምክንያት የነበረ ሲሆን የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ቁጥር 1176/2012፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 የፌዴራል አስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012፣ የማረሚያ ቤት አዋጅ ቁጥር 1174/2012 እና የመገናኛ ብዙኀን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
2012 ዓ.ም
የፌደራል የአሰተዳር ሥነ-ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 የፀደቀ ሲሆን፤ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በአዋጁ በተሰጠው ስልጣን መሰረት መመሪያዎችን ከአስተዳደር ተቋማት ተቀብሎ መመዝገብ፣ ቁጥር መስጠት እና ለህዝብ ተደራሽ ማድረግ ጀመረ፡፡
2014 ዓ.ም
በአዋጅ ቁጥር 1263/2014 መሰረትም ስያሜው ወደ ቀድሞ ስያሜው ፍትሕ ሚኒስቴር እንዲመለስ ተደረገ ሲሆን ተጨማሪ ሀላፊነቶችም ሊሰጡት ችለዋል፡፡
2015 ዓ.ም

የፍትሕ ሚኒስቴር የፌዴራልና የክልል የፍትሕ አካላትን በማስተባበር የሦስት ዓመት የፍትሕ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ወጥቶ ተግባራዊ እንዲሆን አድርጓል፡፡ የዕቅዱ ዋና ዋና አላማዎችም የፍትህ አገልግሎትን ፍጣን፣ ቀልጣፋ፣ ውጤታማ፣ እና ወጪ ቆጣቢ ማድረግ፣ የኅብረተሰብ እምነትን በመገንባት ፍትሕ ተቋማትን የበለጠ ተደራሽና አስተማማኝ ማድረግ፣ የሕግ የበላይነትን እና የሰብዓዊ መብቶችን ጥበቃ ማጠናከር፣ ወንጀልን በመከላከል የመንግሥትን እና የሕዝብን ጥቅም ማስጠበቅ፣ ሰላምን እና ደህንነትን በማረጋገጥ ዘላቂ የልማት ሁኔታ ማመቻቸት ነው።

2016 ዓ.ም
ሚያዝያ 9 ቀን 2016 ዓ.ም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀደቀ፡፡ ፍትሕ ሚኒስቴርም የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ሥርዓቱን በበላይነት የምምራት እና የማስተባበር ኃላፊነት የተሰጠው ሲሆን፤ ፖሊሲው ተግባዊ እንዲሆን በማመቻቸት እና የሽግግር ፍትህ ሂደቱ የተለያዩ ተግባራትን የሚያከናውኑ አካላትን በመደገፍ ተቋሙ የዋና አሰተባባሪነት ሚና ይኖረዋል፡፡
2017 ዓ.ም
ጥር 01/2017 ዓ.ም የንብረት ማመለስ አዋጅን ቁጥር 1364/2017 ጸድቆ ሥራ ላይ ውሏል፡፡ ዋና አላማውም ማንኛውም ሰው ከሕገወጥ ድርጊት ማንኛውንም ዓይነት የኢኮኖሚ ጥቅም ማግኘት እንዳይችል ማድረግ፣ በወንጀል የተገኘ ንብረት ማስመለስን በተመለከተ የወጡ የተበታተኑ የህግ ድንጋጌዎችን አጠቃሎ በመያዝ ለሁሉም የወንጀል አይነቶች የሚችል ሕግ ተግባራዊ ማደረግ እና ምንጩ ያልታወቀ ንብረት በሀገሪቱ የግብር ሥርዓት፣ የውጪ ምንዛሬ፣ የገንዘብ ዝውውር ሥርዓት እና የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ላይ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተጽዕኖ መቆጣጠርና መከታተል ነው፡፡

የቀድሞ የፍትሕ ሚንስትሮች

ከጥር 1900 ዓ.ም. እስከ ሐምሌ 1900 ዓ.ም.
ከ1907 ዓ.ም. እስከ መጋቢት 1910 ዓ.ም.
ከግንቦት 1914 ዓ.ም. እስከ ነሐሴ 1919 ዓ.ም.
ሰኔ 1923 ዓ.ም. እስከ ጥር 1925 ዓ.ም.
ከሐምሌ 7/1935 ዓ.ም. እስከ ሐምሌ 10/1938 ዓ.ም.
ሐምሌ 11/1938 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 29 ቀን 1941 ዓ.ም.
ከሰኔ 30/1941ዓ.ም. እስከ መጋቢት 24/1950 ዓ.ም.
ከመጋቢት 25/1950 ዓ.ም. እስከ የካቲት 1/1953 ዓ.ም.
የካቲት 9/1952 ዓ.ም. እስከ ጥር 10/1955 ዓ.ም.
ከጥር 11/1955 ዓ.ም. እስከ ሚያዝያ 3/1958 ዓ.ም.
ከሚያዝያ 4/1958 ዓ.ም. እስከ መስከረም 1/1962 ዓ.ም.
ከመስከረም 2/1962 ዓ.ም. እስከ የካቲት 25/1966
ከየካቲት 25/1966 ዓ.ም. እስከ የካቲት 23/1967 ዓ.ም.
ከየካቲት 24/1967 ዓ.ም. እስከ ጥቅምት 3/1971 ዓ.ም. እና ከሚያዝያ 11/1975 ዓ.ም. መጋቢት 6/1979 ዓ.ም.
ከጥቅምት 4/1971 ዓ.ም. እስከ ነሀሴ 18/1972 ዓ.ም.
ከመጋቢት 7 ቀን 1979 ዓ.ም. እስከ ግንቦት 19 ቀን 1983 ዓ.ም.
ከ1980 ዓ.ም. እስከ 1983 ዓ.ም.
ከነሐሴ 4/1983 ዓ.ም. እስከ የካቲት 30/1984 ዓ.ም.
ከነሐሴ 25/1984 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 11/1989 ዓ.ም.
ከሰኔ 12/1989 ዓ.ም. እስከ ጥቅምት 5/1994 ዓ.ም.
ከጥቅምት 6/1994 ዓ.ም. እስከ መስከረም 30/1998 ዓ.ም.
ከጥቅምት 1 ቀን 1998 ዓ.ም. እስከ ጥቅምት 19 ቀን 2001 ዓ.ም.
ከጥቅምት 20 ቀን 2001 ዓ.ም. እስከ ሚያዝያ 30 ቀን 2005 ዓ.ም.
ከሚያዝያ 30/2005 ዓ.ም. እስከ ሚያዝያ 17/2012 ዓ.ም.
ከሚያዝያ 17/2010 ዓ.ም. እስከ መጋቢት 3/2012 ዓ.ም.
ከመጋቢት 3/2012 ዓ.ም. እስከ ነሐሴ 12/2012 ዓ.ም.
ከነሀሴ 12/2012 ዓ.ም. እስከ ጥቅምት 8/2017 ዓ.ም.
ክቡር አፈንጉሥ ነሲቡ መስቀሉ
ክቡር አፈንጉሥ ጥላሁን
ክቡር አፈንጉሥ ከተማ
ክቡር አፈንጉሥ መኮንን ደምሰው
ክቡር ፀሐፊ አፈመስፍን አንዳርጋቸው መሣይ
ክቡር ፊታውራሪ ታፈሰ ኃብተሚካኤል
ክቡር ፀሐፊ ትዕዛዝ ወ/ጊዮርጊስ ወ/ዮሐንስ
ክቡር ብ/ጀነራል ዐብይ አበበ
ክቡር ዶ/ር ደጃዝማች ዘውዴ ገ/ሥላሴ
ክቡር ቢትወደድ አስፍሃ ወ/ሚካኤል
ክቡር አቶ ማሞ ታደሰ
ክቡር አቶ አካለወርቅ ሀ/ወልድ
ክቡር ዶ/ር በላቸው አስራት
ክቡር አቶ አማኑኤል ዓምደ ሚካኤል
አቶ ዘገየ አሰፋ
ክቡር ኮሎኔል ወንዳየን ምህረቱ

ሚኒስትር

ክቡር አቶ ቢልልኝ ማንደፍሮ

የኢህዲሪ ጠቅላይ ዐ/ህግ የነበሩ

ክቡር አቶ ሽፈራው ወ/ሚካኤል
ክቡር አቶ ማህተመ ሰለሞን
ክቡር አቶ ወረደ ወልድ ወልዴ
ክቡር አቶ ሀርቃ ሀሮዬ
ክቡር አቶ አሰፋ ከሲቶ
ክቡር አቶ ብርሀን ኃይሉ
ክቡር አቶ ጌታቸው አንባዬ
ክቡር አቶ ብርሀኑ ፀጋዬ
ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
ክቡር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ