7ኛው የፍትሕ ሚኒስቴር እና የክልል ፍትሕ ቢሮዎች የጋራ ጉባኤ በሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በጅግጅጋ ከተማ “ጠንካራ የፍትሕ አካላት ቅንጅት ለተረጋገጠ የሕዝብ አመኔታ” በሚል መሪ ቃል በዛሬው እለት መካሄድ ጀምሯል።
በጉባኤው የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሐና አርአያስላሴ፣የሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ክቡር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ፣የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታዎች፣የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች፣ የክልል ፍትሕ ቢሮ ሃላፊዎች፣የፍትሕ ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛል።
ጉባኤው ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጋራ የሆኑ ጉዳዩች ቀርበዉ ዉይይት የሚደረግበትና የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች የሚቀመጡበት እንደሆነ ተጠቁሟል።