የዐቃቤ ህግ ሙያዊነት አስመልክቶ የፓናል ውይይት ተካሔደ

Panel Discussion Held on the Professionalism of Prosecutors

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር በንቃተ ሕግ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት በየወሩ የሚካሄደው የፓናል ውይይት ለአራተኛ ጊዜ የዐቃቤ ሕግ ሙያዊነት /Professionalism in Prosecution/ በሚል ርዕስ የተቋሙ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም ዐቃብያነ ሕግ በተገኙበት የፓናል ዉይይት ተካሂዷል፡፡

የፓናል ውይይቱን መነሻ ጽሑፍ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህርና የሕግ ባለሙያ የሆኑት ፕሮፌሰር ጥላሁን አቅርበዋል ፡፡በዚህም የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ታሪካዊ ዳራ፣ የዐቃቤ ሕግ ስነምግባር ፣ የሙያ ማሻሻያ፣ በፍትሕ ስርዓቱ ውስጥ የዐቃቤ ሕግ ሚና፣ከክስ እስከ ማስቀጣት ያሉ ሒደቶች ምን መምሰል እንዳለባቸው፣ የሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ ዐቃብ ህጉ ከበላይ አመራሩ ጋር ያለው ግንኙነት ምን መምሰል እንዳለበት እና ዐቃቤያነ ሕግ ከሌሎች የፍትሕ አካላት ጋር የሚኖራቸው ሚና ምን መምሰል እንዳለበት በዝርዝር በፅሁፉ ተዳሷል፡፡

የቀረበውን ዳሰሣዊ ጥናት ተከትሎ ተሳታፊዎች ጥያቄ ፣አስተያየት እና ቢብራሩ ያሏቸውን ሀሳቦች አነስተው በፕሮፌሰር ጥላሁን ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

በሶስተኛዉ የፓናል ዉይይት የሕግ ሚና ማኅበራዊ ትስስርን በመፍጠር/በማጠናከር እና የሽግግር ፍትሕ “በሚል የመወያያ ርዕስ የፓናል ዉይይት መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን በቀጣይም መሰል የፓናል ዉይይቶች ወር በገባ በመጀመሪያ ሳምንት መካሄዳቸው የሚቀጥል መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

Tagged Under: Addis Ababa University civil liberties Criminal Procedure Discussion Due Process ethics federal federal ministry of justice fundamental rights general Human Rights Judicial System Justice legal Legal ethics Legal Reform Legal Training ministry panel panel discussion professional development professionalism Prosecutor Prosecutor General prosecutorial prosecutorial professionalism Rule of Law Stakeholder Engagement transitional justice
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች