የፍትሕ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ

የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮጵያ ያለውን የፍትሕ ስርዓት ለማሻሻልና ለመለወጥ የሚያስችል የሀገር አቀፍ የፍትሕ ዘርፍ የትራንስፎርሜሽን እቅድ ቀርፆ ወደ ስራ ገብቷል። ይህ ታላቅ ተነሳሽነት በስፋት እና በወሰን ሁሉን አቀፍና የተሟላ ነው። በፌደራልም ሆነ በክልል ደረጃ የሚከናወነውን ምርመራ፣ ክስና የማረም ስራ ይሸፍናል። የዚህ ዕቅድ ዋና ዓላማ፣ በ2012 ዓ/ም የፍትሕ ፍላጎትና እርካታ በኢትዮጵያ በሚል በሂል በተካሄደው ጥናት እንዲሁም በ2013 ዓ/ም በኢትዮጵያ የወንጀል ፍትሕ ስርዓት ላይ የተደረገ የምርመራ ጥናትን ጨምሮ በተለያዩ ጥናቶች ላይ የተስተዋለውን የህብረተሰቡን የፍትሕ ዘርፍ እርካታ እና አመኔታ ለማረጋገጥ ነው። የሶስት አመት የፌዴራል ፍትሕ ዘርፍ የትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈፃፀም የተጀመረው ከሐምሌ 2015 ዓ/ም ጀምሮ ነው። እቅዱ 10 ዋና ዋና ዓምዶችን ይሸፍናል። እነዚህም የሚከተሉት ናቸው፡-

የመሰረተ-ማህበረሰብ ፍትሕ አገልግሎት

ይህ ተነሳሽነት በህብረተሰቡ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች የሚያጋጥሙ አለመግባባቶችን በህብረተሰቡ የባህላዊ ወይም ልማዳዊ አለመግባባቶች መፍቻ ስርአቶች በመጠቀም ህዝብን መሰረት ያደረገ ፍትሕን እውቅና ለመስጠትና ለማበረታታት የሚደረግ ጥረት ነው።

የፍትሕ ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎችን ማጥራት

በፍትሕ ዘርፍ ያሉ ባለሙያዎችን በስነ ምግባር፣ በብቃት እና በሃብት ላይ ተመስርቶ ነፃ ምርመራ ማካሄድ ታሳቢ ያደርጋል።

ቴክኖሎጂ

በፍትሕ ስርዓት ውስጥ ቴክኖሎጅን አጠቃቀምን ማሻሻል፣ ማዳበር እና ውጤታማ ማድረግ ማለትም የዲጂታል ፍትሕ ማሻሻያ ማድረግ ነው፡፡

የወንጀል፣ ፍትሐብሔር እና አስተዳደራዊ ፍትሕ በአዲስ አቅጣጫ

አዲሱ ረቂቅ የተሻሻለው የወንጀል ስነ ስርዓት ሕግ ፀድቆ አዳዲስ የለውጥ ሂደቶች ይተዋወቁበታል ተብሎ ይጠበቃል፤ በተጨማሪም የአስተዳደር ስነ ስርዓት አዋጁን በመተግበር በአስተዳደር ፍትሕ ላይ ስር ነቀል ለውጥ ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል።

የሕግ መሰረተ ትምህርትን ማጠናከር እና የነጻ የሕግ ድጋፍ

መጠነ ሰፊ የሕግ መሰረተ ትምህርት እና ኤክስቴንሽን ፕሮግራሞችን ማካሄድ፣ ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት እና አፈፃፀሙ በአዲስ ስትራቴጂ እና ሕግ ላይ ተመስርቶ እንደሚሻሻል ይጠበቃል፡፡

ዘመናዊ አማራጭ ያለመግባባት መፍቻ ስርአቶች ማስፋፋት

ኢትዮጵያን የአማራጭ አለመግባባት መፍቻ ማዕከል ማድረግ እና ዘመናዊ የአማራጭ ያለመግባባት መፍቻ ስርአቶች ለማቋቋምና ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል አዲስ ሕግ ማውጣት ይጠበቃል።

በፍትሕ ዘርፍ አካላት መካከል የቀጥታ እና የተዋረድ ቅንጅትን ማሻሻል

የፌደራል ፍትሕ አካትን በክልሎች ተደራሽነት ማጠናከር

ተገቢ እና ውጤታማ የህዝብ ተሳትፎ ማስፈን

የፍትሕ ዘርፉን አደረጃጀት ማሻሻል፣ ዘርፉን ተአማኒ፣ ሳቢና ምቹ ማድረግ ናቸው፡፡

ዋና ዋና ተግባራት

የሽግግር ፍትሕ በኢትዮጵያ

የሕግ እና ተቋማዊ ማሻሻያዎች

ዜና

“የርትዕ የፍትሕና የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ሪፎርም አስፈላጊ ነዉ” ክቡር ዶክተር ኤርሚያስ የማነብርሃን በፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ • “Reform is Necessary to Ensure Fairness, Justice, and the Rule of Law” Honorable Dr. Ermias Yemanebirhan, State Minister of Institutional Development and Reform Sector at the Ministry of Justice

የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኤርሚያስ የማነብርሀን ከፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ የኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት ከሉዊስ አንቶኒዮ ሶቼት ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ • State Minister for Institutional Building and Reform, His Excellency Dr. Ermias Yemanebrhan, Discusses Bilateral Issues with the Country Director of the French Development Agency (AFD) in Ethiopia, Mr. Louis-Antoine Souchet

ከነሐሴ 23-24 (2015 ዓ.ም በተካሔደው የፍትሕ ሚኒስቴር እና የክልል ፍትሕ ቢሮዎች) ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተቋማት የጋራ መድረክ ላይ የክልሎች የፍትሕ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተደረገ • Regional Justice Transformation Plans Presented and Discussed at Joint Forum of the Ministry of Justice and Regional Justice Bureaus/Attorney General Institutions Held August 23-24, 2015 EC

ጽሑፎች

ቪዲዮዎች