የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፍትሕ ዘርፉን በተመለከተ ሰፊ የሕግ ማሻሻያ ሥራዎች የተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የታሰሩ ተጠርጣሪዎችና ታራሚዎችን በሚመለከት በሰጡት ምላሽም ከዚህ በፊት ባልተለመደ ሁኔታ የፓርላማ አባላት እስረኞችን በመጎብኘት የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታቸውን መመልከታቸው በዘርፉ የተደረገውን ለውጥ እንደሚያመላክት አንስተዋል፡፡ ከክስ ጋር በተገናኘ መንግሥት ሁል ጊዜም ቢሆን ራሱን ክፍት ማድረግና አሰራሩን መፈተሽ እንደሚገባው በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡
በሌላ በኩል ባሕላዊ ፍርድ ቤቶችን እውቅና በመስጠት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን በማመልከት በፍትሕ ሚኒስትር እና በፖሊስ የዘርፉን ሪፎርም ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመተግበር ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
በፍርድ ቤቶች በኩል የሚሰጡ አገልግሎቶች እንዲሻሻሉ በቴክኖሎጂ የማዘመን ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አንስተዋል፡፡