የፍትሕ ሚኒስቴር ሥልጣን እና ተግባር

የወንጀል ሕግ ጕዳዮችን በሚመለከት
- የወንጀል ፍትሕ ፖሊሲን ማዘጋጀት እና አፈጻጸሙን ማስተባበር፤
- በፌዴራል ፍርድ ቤት ሥልጣን ሥር የሚወድቁ የወንጀል ጕዳዮችን ምርመራ የመምራት፣ ውሳኔ የመስጠት፣ የወንጀል ክስ በመመሥረት በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ተገቢውን ክርክር በማድረግ አጥፊዎችን ተጠያቂ ማድረግ፤
- በወንጀል የተገኘ ሀብትን መመርመር፣ ማሳገድ እና ማስወረስ፤

የፍትሓ ብሔር ጕዳዮችን በሚመለከት
- የፌዴራል መንግሥቱን እና ተቋማትን ፍትሓ ብሔራዊ ጥቅም፣ በሀገር ውስጥ እና በዓለም ዐቀፍ መድረክ በፍርድ ቤት እና ከፍርድ ቤት ውጭ ባሉ አማራጮች በማስከበር የሕዝብ እና የመንግሥት ጥቅምን ማስጠበቅ፤
- የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች እርስ በእርስ ያላቸውን የፍትሓ ብሔር አለመግባባት የሕዝብን እና የመንግሥትን ጥቅም በሚያስከብር አግባብ መፍታት፤

የአስተዳደር ፍትሕ ጕዳዮችን በሚመለከት
- የፌዴራል መንግሥቱ ሕጎች ወጥነት ባለው አግባብ በትክክል መተግበራቸውን ማረጋገጥ፤
- የፌዴራል መንግሥት ተቋማት የሚያወጧቸው መመሪያዎች አግባብ መሆናቸውን ማረጋገጥ እና ለሕዝብ ተደራሽ እንዲሆኑ ማስቻል፤

የሕግ አገልግሎት ጕዳዮችን በሚመለከት
- የፌዴራል መንግሥቱን በሕግ ጕዳዩች ላይ ማማከር፤
- በፌዴራል መንግሥቱ የሚወጡ ሕጎችን የማርቀቅ እና የማረም ኀላፊነት መውሰድ፤

የሰብአዊ መብት ጕዳዮችን በሚመለከት
- ለአቅመ ደካማ ዜጎች ነጻ የሕግ ድጋፍ መስጠት እና አገልግሎት አሰጣጡን ማስተባበር፤
- የሰብአዊ መብት አከባበርን ማረጋገጥ እና ዓለም ዐቀፍ ሪፖርቶችን ማቅረብ፣ በኢትዮጵያ ላይ የሚቀርቡ ሰብአዊ መብትን ለሚመለከቱ ዓለም ዐቀፍ ክሶች ምላሽ መስጠት፤