የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች ጋር የወንጀል ምርመራ፣ ክስና ክርክር ስራዎች ውጤታማነትን ለማሳደግ ያለመ ውይይት አድርገዋል፡፡
ባለፉት ዓመታት የወንጀል ምርመራ፣ ክስና ክርክር ስራዎች ውጤታማነት ለማሳደግ ሁለቱ ተቋማት በጋራ ባከናወኗቸው ተግባራት የተገኙ ዘርፈ ብዙ ውጤቶችን ለማስጠበቅ በትብብር መሥራት እንደሚገባ እንዲሁም የታዩ ውስንነቶችን በመቅረፍ በቅንጅት ተናቦ መሥራት እንደሚገባ በውይይቱ ወቅት ተመላክቷል፡፡
ውይይቱን መነሻ በማድረግም የወንጀል ምርመራ፣ ክስና ክርክር ስራዎች ቅልጥፍና፣ ጥራት፣ ውጤታማነትና ተደራሽነት ለማሻሻል ሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ ሚና የላቸው በመሆኑ የጋራ የሆነ አሠራር ስርዓትን መዘርጋት፣ አደረጃጀቶችን ማናበብ፣ የክትትልና ግምገማ ስርዓት መዘርጋት እና ቅንጅታዊ አሠራርን ማጎልበት እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
በውይይቱ የፍትሕ ሚኒስቴር እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ተገኝተዋል።