ቅሬታዎን ያቅርቡ ወይም አስተያየትዎን ይስጡ

የፍትሕ ሚኒስቴር የሕግ፣ የወንጀል እና የአስተዳደር ጕዳዮችን በሚመለከት የዜጎችን አስተያየት በአክብሮት ይቀበላል። ሥጋትዎን ለማጋራት፣ አስተያየትዎን ለመስጠት ወይም ቅሬታዎን ለማቅረብ ከታች ያሉትን ቅጾች ይጠቀሙ። ያቀረቡት ጥቆማም ሆነ ጥያቄ ተገምግሞ ለተጨማሪ ርምጃ ወደሚመለከተው ክፍል ይተላለፋል።
  • ሕጋዊ ወይም የወንጀል ጕዳዮች፦ ከአጠቃላይ የወንጀል ድርጊቶች ወይም ከንብረት መልሶ ማግኛ (ጥቆማ) ጋር የተያያዙ ጕዳዮችን ሪፖርት ያድርጉ።
  • አስተዳደራዊ ጕዳዮች፦ ስለ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አገልግሎቶች፣ ስለ ክስ ወይም አጠቃላይ አስተዳደራዊ ጕዳዮች በሚመለከት ያሉብዎን ሥጋቶች ያቅርቡ።

የቀረቡ ጥቆማዎች፣ አስተያየቶች ወይም ጥያቄዎች በምሥጢር የሚያዙ ሲሆኑ፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ምላሽ ይሰጥባቸዋል።

ሕጋዊ ወይም የወንጀል ጕዳዮችን በሚመለከት የሚቀርቡ አስተያየቶች የሚቀርቡበት ቅጽ

ዜጎች በወንጀል ጕዳዮች ላይ ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም አስተያየት እንዲሰጡ የሚያስችላቸው ሲሆን፣ የሚሰጡት አስተያየትም ወደሚመለከተው ክፍል የሚተላለፍ ይሆናል።


አስተዳደራዊ ጕዳዮችን በሚመለከት የሚቀርቡ አስተያየቶች የሚቀርቡበት ቅጽ

የአገልግሎት አሰጣጥን፣ ክስን ወይም አስተዳደራዊ ጕዳዮችን ጨምሮ ስለ ፍትሕ ሚኒስቴር አገልግሎቶች አስተያየቶችን እና ቅሬታዎችን ይሰበስባል።