በትላንትናው እለት የጀመረው በፍትሕ ሚኒሰቴር እና በ I-Arb Africa በጋራ አዘጋጅነት እየተካሄ የሚገኘው 11ኛው የምስራቅ አፍሪካ ዓለም ዓቀፍ የግልግል ዳኝነት ኮንፍረንስ ዛሬም እንደቀጠለ ነው፡፡
ምንም እንኳን በአሁኑ ወቅት የግልግል ዳኝነት ሥርዓትን በማሳደግና ተጠቃሚ ክመሆን አኳያ የሚታወቁት በአውሮፓ ሀገራት፣ በኢሲያ እና አሜሪካ የሚገኙ ድርጅቶች ቢሆኑም፣ እንደ አፍሪካ ዘርፉ እንብዛም እውቅና አግኝቶ ያደገ ባለመሆኑ የምስራቅ አፍሪካ ዓለም ዓቀፍ የግልግል ዳኝነት ኮንፍረንስን ጨምሮ መሰል ዝግጅቶች በ I-Arb Africa እንዲሁም በሎሎች መሰል ድርጅቶች አማካኝነት የግልግል ዳኝነት ዘርፍ በአህጉሪቱ ብሎም በምስራቅ አፍሪካ ማስተዋወቅ እና ማሳደግ ዓላማ ላይ ያተኮሩ እንቅስቃሴዎች ሊደገፉ እንደሚገባ በኮንፍረንሱ ተጠቁሟል፡፡
ይህንንም መነሻ በማድረግ በኮንፍረንሱ ላይ ከትላንትና ጀምሮ በግልግል ዳኝነት ጉዳዮች ላይ የፓናል ውይይት ከተለያዩ ፓናሊስቶች ጋር ተካሂዷል፣ በጉዳዩች ላይ ያሉ ክፍተቶች እንዲሁ ተነስተው የመፍትሄ ሀሳቦች ተስጥቶባቸዋል፡፡