የፍትሕ ሚኒስቴር የሰው ሀብት አቅምን ማሳደግ የሚያስችሉ የሪፎርም ተግባራትን በማከናወን ላይ መሆኑ ተገለፀ

Ministry of Justice Undertaking Reform Activities to Enhance Human Resource Capacity

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ፣ ትምህርትና ሥልጠና ዳሬክቶሬት ከSOPHOS AFRICA የልማት ድርጅት ጋር በመተባበር በተዘጋጀ የአቅም ግንባታ ትምህርት ላይ ተሳትፈው መሠረታዊ የአመራርነት /የሊደርሽፕ/ ክህሎት ሥልጠና ለወሰዱ መካከለኛ አመራሮች እውቅና ተሰጥቷል፡፡

ከፍትሕ ሚኒስቴር የተለያዩ የስራ ክፍሎች ለተወጣጡና ለተከታታይ 6 ሳምንታት ለ18 ሰዓታት መሠረታዊ የአመራርነት ክህሎት ሥልጠና ወስደው ላጠናቀቁ መካከለኛ አመራሮች እውቅና የመስጠት መርሀ-ግብር በትላንትናው እለት የተካሄደ ሲሆን፤ በመድረኩ ላይ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ኤርምያስ የማነብርሃን (ዶ/ር) እንደተናገሩት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በዋነኛነት የሰው ሀብት አቅምን ማሳደግ፣ አሠራርና ስርዓትን ማሻሻል፣ እንዲሁም የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማትን መገባንባት የሚያስችሉ የሪፎርም ተግባራትን በማከናወን ላይ መሆኑን አስታውሰው ከSOPHOS AFRICA ጋር በመተባበር በሞጁል ዝግጅት፣ በትምህርት አሰጣጥና ሥልጠናው ከወሰደው ጊዜ አንፃር ልዩ ዝግጅት ተደርጎ ውጤታማ የሆነ የሊደርሽፕ ሥልጠና ለአመራሩ እንዲሰጥ መደረጉን ገልፀዋል፡፡

አያይዘውም ሥልጠናው ሀላፊነታቸውን በአግባቡ የሚወጡ አመራሮችን ለማፍራት የሚያግዝ በመሆኑ ፍትሕ ሚኒስቴር ላቅ ያለ የስራ ባህል ያላቸው ሰራተኞችን ለመፍጠር በሥልጠና አቅም የመገንባት ተግባሩን ከSOPHOS AFRICA ጋር አጠናክሮ እንዲቀጥል የሚደረግ መሆኑን ጠቅሰው፤ ወቅቱ የራስን አቅም መገንባት የሚጠይቅ በመሆኑ ይህ ሥልጠና እራስን በራስ የመቻል ብቻ ሳይሆን እንደ ሀገር ሁሉም ሰው በቀጣይነት የተሻለ ህይወት እንዲኖረው ለማድረግ መልካም አስተዋፅኦ የሚያበረክት መሆኑን በመግለፅ፤ ሥልጠናውን የወሰዱ አመራሮች ያገኙትን እውቀት ወደ ተግባር ለውጠው የተሻለ ስራ ማከናወን እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል፡፡የፍትሕ ሚኒስቴር ተለያዩ ግብዓቶችን በማሟላት ይህ የሊደርሽፕ ሥልጠና እንዲሰጥ ማድረጉንም ገልፀዋል፡፡

ሥልጠናውን በአጋርነት የሰጠው የ SOPHOS AFRICA ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ደስታ ሀሊሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው ድርጅታቸው በአፍሪካ ውስጥ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመግታት ቀጣይነት ያለው እድገት እንዲኖር የማድረግ ዓላማን ይዞ በመመስረት የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ ሕግና ፍትሕ ከሌለ የተሻለ ሀገር ሆነ እድገት ሊኖር ስለማይችል ለጉዳዩ ቅድሚያ በመስጠት ለሕግ የበላይነት መረጋገጥ ትኩረት ሰጥተው የሚሰሩ ዜጎችን የማፍራት ስራን ለማከናወን ከፍትሕ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

የአቅም ግንባታ ሥልጠናውን የተከታተሉት አመራሮች በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት ሥልጠናው የመሪነትን ጥበብ ወደ ተግባር ቀይሮ ማየት ያስቻለ ተሞክሮ ያገኙበትና በቀጣይነት የተሻለ ስራን በቀላል መንገድ ለማከናወን የሚያስችላቸውን እውቀት ያገኙበት መሆኑን ገልፀዋል፡፡

Tagged Under: activities administration Africa building capacity capacity development civil service reform development development organization governance human institutional Institutional Reform Leadership Leadership Development Leadership Training legal Legal Reform management skills middle managers public Public Administration reform resource Rule of Law Training
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች