በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትህ የህግ ረቂቆች ዙሪያ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የነበረው አለም አቀፍ ኮንፍረስ ተጠናቀቀ

International Conference on Transitional Justice Draft Laws in Ethiopia Concludes

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ከInstitute for Security Studies (ISS) ጋር በመተባበር በሽግግር ፍትሕ ረቂቅ ህጎች ላይ በአዲስ አበባ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የነበረው ዓለም ዓቀፍ ኮንፍራንስ በዛሬው ዕለት ተጠናቋል፡፡

በተካሄደው ዓለም ዓቀፍ ኮንፍረንስ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የአለም ዐቀፍ የወንጀል ፍትሕ የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ቤዝ ቫን ስቻክ ለኮንፍረንሱ መሳካት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴርን አመስግነው ይህ በመንግሥት ደረጃ የታየው ቁርጠኝነት ወደ ሽግግር ፍትሕ ስርዓት ለመግባት የሚያስችለውን በር የከፈተ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከብዙ ጥረቶች በኋላ ተግባራዊ ለመሆን የተቃረበው የኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ከፍተኛ የሆኑ ወንጀሎችን የፈፀሙ አካላት ተጠያቂ የሚሆኑበትና ፍትሕ በሀገሪቱ ሰፍኖ ህዝቡ በሰላም የሚኖርበትን መልካም አጋጣሚ የሚገኝበት ስመለሆኑ ያላቸውን እምነት ገልፀው፤ ለዚህ ወሳኝ የሆነ ጉዳይ ውጤታማነት ከተለያዩ ሀገራት የመጡት ባለሙያዎች ላበረከቱት አስተዋጥኦ እንዲሁ አድናቆታቸውን ገልፀዋል፡፡

ኮንፍረንሱ በዛሬ ውሎው በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ረቂቅ ህጎች ዙሪያ ከተለያዩ የአለም ሀገራት ተወክለው የመጡ የዘርፉ ባለሙያዎች በትላተናው ዕለት ከተጀመረው የቡድን ውይይት ቀጥለው የነበሩ ግኝቶችና የተሰጡ ምክረ ሀሳቦች ቀርበው ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ በሁሉም የባለሙያዎቹ ቡድን የተሰጡ ገንቢ ትችቶች፣ ቁልፍ የሆኑ ግኝቶች እና ምክረ ሀሳቦች በዝርዝር የቀረቡ ሲሆን እነዚህም፤ በድጋሚ መታየት የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች፣ አዋጅና ህጎቹን ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶች እንዲሁም ህጉ የተጎጂዎችን እና አጠቃላይ የማህበረሰቡን ፍላጎቶች ሊያሟላ የሚችል አቅጣጫን የሚያመለክቱ አስተያየቶች ቀርበዋል፡፡

በተያያዘም የቡድን ውይይቶቹ የወንጀል ተጠያቂነትን ማስፈን፣ እውነት ማፈላለግ፣ ምሕረት እና የተቋማት ግንባታ በሚል በተቀመጡ የኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ምሶሶዎች አንዱ ከሌላኛው ጋር ተደጋግፎ በጥምረት ሊተገበር የሚችልበትን አቅጣጫ ዓለም ዓቀፍ ተሞክሮዎችን በመጥቀስ ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉበትን መንገድ አመልክተዋል፡፡

በአጠቃላይ ይህ በሽግግር ፍትሕ ረቂቅ ህጎች ላይ የተደረገው ዓለም ዓቀፍ ኮንፍረንስ የሕግ ረቂቆቹ ተጠናቅቀው የሚፀድቁበትን ቀጣይ ተግባራት ያመላከተ ከመሆኑም በላይ በሀገር ደረጃ፣ እርቅ እና ዘላቂ የሆነ ሰላም በተለይም ተጎጂ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ፍትሕ የሚደርስበትን መንገድ በማመላከት ረገድ ከፍተኛ የሆነ ውጤት የተገኘበት መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

በኮንፍረንሱ የመዝጊያ ዝግጅት ላይ በመገኘት መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኤርምያስ የማነብርሀን በበኩላቸው ዓለም ዓቀፍ ባለሙያዎቹ ሀገሪቱ ወደ ሽግግር ፍትሕ እያደረገች የምትገኘውን ጉዞ ለማገዝ በመምጣታቸው ምስጋናቸውን አቅርበው ለወደፊቱም አብሮ ለመሥራት ፍላጎት እንዳለ ገልፀው፤ በውይይት መድረኩ ላይ ከባለሙያዎቹ የተሰጡት ግብረመልሶችና የተገኙት ልምድና ተሞክሮዎች አንድ ላይ ተቀምረው ለሚዘጋጁት ህጎችና አዋጆች እንደ ግብዓት የሚያገለግሉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም የኮንፍረንሱ ተሳታፊዎች የታሪካዊውን የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በመጎብኘት መድረኩ ተጠናቋል፡፡

Tagged Under: act conference decree draft draft law ecu federal institute of justice and law federal justice and law institute fundamental law institute international International Conference itu Justice law Law Enforcement Laws legislation National Police Policy proclamation Regulation Security statute studies transit transition transitional transitional justice
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች