መድረክ እየተካሄደ ይገኛል
ከዳኝነት የውጭ አማካሪ ምክር ቤት አባላትና የተለያዩ የሕግ ምሁራን ጋር የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲን መሠረት አድርጎ በሚቋቋም ልዩ ችሎት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከቀን 21/03/2017 እስከ 22/03/2017 ዓ.ም ለሁለት ቀናት የሚቆይ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
የመድረኩ ዓላማ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ን መነሻ በማድረግ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በተቋቋመው የሕግ አርቃቂ ኮሚቴ አባላት የተዘጋጀው ረቂቅ የልዩ ችሎት ማቋቋሚያ አዋጅ .ላይ ከሕግ ምሁራን ግብዓት ለማሰባሰብ ነው፡፡
ረቂቅ አዋጁን የሽግግር ፍትሕ የተቋማት ቅንጅታዊ አመራር መድረክ ሴክሬታሪያት ስር የተዋቀረ የባለሙያዎች ቡድን ያዘጋጀው ሲሆን የቡድኑ ባለሙያዎች በግብዓት ማሰባሰቢያ መድረኩ ላይ ተገኝተው ተሳታፊውን በማወያየት ላይ ይገኛሉ።
ከዚህ ቀደም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከፌደራል ፍርድ ቤት አመራሮች እና ዳኞች ጋር የምክክር መድረክ መደረጉ የሚታወስ ነው። በቀጣይም በዚሁ ረቂቅ ሕግ ላይ አምስት የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረኮችን ለማካሄድ ዕቅድ ተይዟል።
ምንጭ:-የሽግግር ፍትሕ የተቋማት ቅንጅታዊ አመራር መድረክ ሴክሬታሪያት