የኢፌዲሪ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቆ ወደ ትግበራ ምዕራፍ መሻገሩ ይታወቃል፡፡ የፍትሕ ሚኒስቴርም በፖሊሲው የተጣለበትን የማስተባበር ኃላፊነት ለመወጣት ያስችለው ዘንድ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን ባሳተፈ መልኩ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲው የትግበራ ምዕራፍ የሚመራበትን ፍኖተ ካርታ ረቂቅ ሰነድ የማዘጋጀት ስራ አጠናቋል፡፡ በሚቀጥሉት ቀናትም በተዘጋጀው ረቂቅ ፍኖተ ካርታ ላይ የግብዓት ማሰባሰቢያ የምክክር መድረኮች ይካሄዳሉ፡፡ በመድረኮቹ የሚነሱ አስተያየቶችን በማካተት የመጨረሻው ሰነድ በተለያዩ ዘዴዎች ለመላው ሕዝብ የሚጋራ ሲሆን የማስግበሪያ ፍኖተ ካርታው በአጭር ጊዜ ውስጥም በተሟላ ሁኔታ ወደ ትግበራ እንደሚገባ ይጠበቃል፡፡
በመሆኑም ከዚህ መረጃ ጋር ተያይዞ በቀረበው ረቂቅ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ማስተግበሪያ ፍኖተ ካርታ ላይ አስተያየት ለመስጠት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው አስተያየቱን በኢሜይል አድራሻ [email protected] ላይ መላክ የሚችል መሆኑን በአክብሮት እየገለፅን፣ ረቂቅ የፍኖተ ካርታውን ከዚህ በታች የተጠቀሰውን ሊንክ በመጫን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡