ይህ አረንጓዴ የጥናት ወረቀት (የፖሊሲ ማዕቀፍ አማራጮች ሰነድ) በሽግግር ፍትሕ ዙርያ ያሉ የፖሊሲ አማራጮችን ለውይይት መነሻ እንዲሆኑ የቀረቡበት ሰነድ ነው።
ሰነዱን መነሻ በማድረግ በሽግግር ፍትሕ ዙርያ በሀገር-አቀፍ ደረጃ ውይይት እና ክርክሮችን በስፋት በማካሄድ – በሃገራችን ነባራዊ ሁኔታ የተሻሉ አማራጮችን በመለየት እና የፖሊሲ መነሻ ሃሳቦቹን በማዳበር በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ማዕቀፍ እንዲኖር ለማድረግ ታስቧል።
ከዚህ አንፃር በቀጣይ በአገር-አቀፍ ደረጃ ተከታታይ የፖሊሲ ውይይት መድረኮች የሚዘጋጁ ሲሆን በቅድሚያ ለዚህ መነሻ ይሆን ዘንድ ይህን ሰነድ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበታል።
ሰነዱን ተመልክታችሁ ለሚኖራችሁ ማንኛውም አስተያየት የምናመቻቻቸው የውይይት መድረኮች እንደተጠበቁ ሆነው በኢሜይል አድራሻ [email protected] ወይም በፖስታ ሳጥን ቁጥር 1370 ለፍትሕ ሚኒስቴር መላክ የሚቻል መሆኑን በማክበር እንገልጻለን፡፡
በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ/ ሊንክ/ በመጫን ሙሉ ሰነዱን ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡