የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አማራጭ ሃሳብ ላይ ሲደረጉ የነበሩት ሀገር አቀፍ የግበዓት ማሰባሰቢያ የውይይት መድረኮች መጠናቀቃቸውን ተከትሎ የፖሊሲውን አስፈላጊነት፤ የውይይት መድረኮቹን ሂደት፣ ግኝቶች እና በቀጣይ ስለሚከናወኑ አበይት ተግባራት እንዲሁም በሽግግር ፍትሕ ፖሊሲው እና ከሀገር አቀፉ የምክክር ኮሚሽን ተልዕኮ ጋር ተያይዞ በሚነሱ ጥያቄዎች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል፡፡
በመሆኑም ነገ ማክሰኞ ነሃሴ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ጀምሮ በፍትሕ ሚኒስቴር በሚካሄደው በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ፈቃድ ያለው ማንኛውም የሚዲያ ተቋም ባለሙያዎችን ወደ ተጠቀሰው ቦታ በመላክ ጉዳዩ በቂ የዜና ሽፋን እንዲያገኝ ያደርግ ዘንድ ግብዣ እያቀረብን በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ለመሳተፍ የተመደበው ባለሙያ ከላከው የሚዲያ ተቋም የተሰጠ መታወቂያ ወይም የትብብር ደብዳቤ ይዞ መቅረብ ያለበት መሆኑን አንገልጻለን፡፡