የፌዴራል ሕጎች ተፈጻሚነት ዳይሬክቶሬት

የፌደራል ሕጎች ተፋፃሚነት ክትትል የሥራ ክፍል በሀገራችን ውስጥ የፌደራል ሕጎች ወጥነት ባለው መልኩ መተግበራቸውን ያረጋግጣል። ይህንን ለማድረግ በርካታ የክትትል መንገዶችን በመጠቀም የሕጎች አፈጻጸም ላይ የሚታዩ ልዩነቶችን እና መዛነፎችን ይለያል። በተጨማሪም የፌደራል ሕጎች በተግባር እንዴት እየተተገበሩ እንዳሉ በመከታተል፣ ክፍተቶችን፣ ተግዳሮቶችን እና የአፈጻጸም ችግሮችን በመለየት ወቅታዊ ማስተካከያዎችን፣ የእርምት እርምጃዎችን እና የፖሊሲ ምክሮችን እንዲወሰዱ ያስችላል። እንዲሁም የተቋማትን ምርጥ ተሞክሮዎችን በማጋራት የሕግ አተገባበር ወጥነት እንዲኖረው ያደርጋል። በተመሳሳይ የአስተዳዳር ፍትሕን ለማስፈን የሚያስችሉ የክትትል እና የተቋማት አቅም ግንባታ ተግባራትን ያከናውናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አስፈፃሚ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሥራቸውን በሕግ መሠረት ማከናወናቸውን ያረጋግጣል፡፡ ይህ የየክትትል ሥራ የፌደራል አስፈፃሚ መሥሪያ ቤቶች አሠራር፣ ውሳኔዎች እና ድርጊቶች በሕግ የተደገፉ መሆናቸውን በማረጋገጥ አስፈፃሚው በሕግ ወሰን ውስጥ እንዲሠሩ ያደርጋል። የሥራ ክፍሉ የሚሰራው የቅድመ ክትትል እና ጥብቅ ኦዲት ለፌደራል ሕጎች ወጥነት ያለው አተገባበርን ልህቀትያስጠብቃሉ፡፡

የሥራ ክፍሉ የክትትልና የኦዲት ግኝቶችን በተመለከተ ዝርዝር ሪፖርቶችን በማዘጋጀት ግልጽነትና ተጠያቂነትን ያረጋግጣል፤ እነዚህንም ሪፖርቶች ለሕግ አውጪዎችና ለሕዝብ ይፋ ያደርጋል። ቀጣይነት ባለው እና በጥብቅ ክትትል አማካኝነት የሥራ ክፍሉ ሕጎች በፍትሃዊነት እንዲተገበሩ አስተዋፅዖ ያደርጋል። በዚህም የሕግ የበላይነት እንዲከበር፣ የሕዝብ እምነት እንዲጠናከር እና የመንግሥት ተቋማት በሕግ መሠረት እንዲሰሩ ያደርጋል፡፡

የሥራ ክፍሉን ያግኙ

የሥራ ክፍሉ መሪ

ሀወኒ ታደሰ

ዳይሬክተር

News From Federal Laws Enforcement Directorate