በተጠናቀቀው የ2015 በጀት አመት 9 ዓዋጆች፣ 3 ደንቦችንና 7 መመሪያዎችን ማርቀቅ መቻሉ ተገለፀ

Drafting of 9 Proclamations, 3 Regulations, and 7 Directives Achieved in the Completed 2015 Budget Year

የኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የመንግሥት ሕግና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ የ2015 የበጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፓረት ሲቀርብ በበጀት አመቱ 9 ዓዋጆችን፣ 3 ደንቦችንና 7 መመሪያዎችን በድምሩ 19 ሕጎችን የማርቀቅ ስራ መሰራቱ ተገልጿል።

ሪፓርቱን ያቀረቡት በፍትሕ ሚኒስቴር የፌደራል ህጎች ተፈፃሚነት መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ትብለጥ ቡሽራ ተቋሙ በአዋጅ ከተሰጡት ተግባርና ሀላፊነቶች ውስጥ የመንግሥት ሕግና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ በርካታ ህጎችን የማስፈፀም ኃላፊነት ተጥሎበታል ብለዋል።

በመሆኑም አነዚህን ሀላፊነቶች በመወጣት በኩል በተጠናቀቀዉ በጀት ዓመት በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን የገለፁት ዳይሬክተሯ የወንጀል መከላከል አቅምን ማሳደግን በተመለከተ ለ395 የወንጀል መከላከል ፈፃሚ ተቋማት ሥልጠና መሰጠቱን ገልፀዋል።

ከይቅርታና አመክሮ አፈፃፀም ክትትልና ውጤታማነትን ማሻሻል ለውሳኔ ከቀረቡ 1162 ጥያቄወች ውስጥ ውሳኔ አግኝተው 1159 ከማረሚያ ቤት የወጡ መሆናቸውንና ቀሪ 3ቱ ከእድሜ ልከ እስራት ወደ 25 ዓመት ዝቅ እንዲል መደረጉን ገልፀዋል።

ህገወጥ የሰዎች ዝውውር መከላከልን በተመለከተም የፌደራሉ የጥምረት ጉዳዬችን ከተጠሪ ግለሰቦች በላይ በከፍተኛ የተቋም ሀላፊወች እንዲመራ መደረጉን በሪፓርቱ ገልፀዋል።

የመንግሥትና የሕዝብን ጥቅም በማስጠበቅ በኩልም በስሩ በተከናወኑ በግልግል ዳኝነትና ድርድር በበጀት አመቱ የዓለም ዓቀፍ የድርድር በእንግሊዝ በህንድና በግሪክ ተቋማት የቀረበውን ክስ ወደ ድርድር እንዲመጣ መደረጉንና በዚህም 10 ሚሊዬን ዩሮ በላይ ከቀረበው ክስ 6.3 ዩሮ በድርድር ማስቀረት መቻሉንና ሌሎች መሰል ተግባራትን በማከናወን አገሪቱ ልታጣው የነበረ በርካታ ገንዘብን ማዳን መቻሉን የተገለፀ ሲሆን የፍትሐብሔር የፍርድ ቤት ክርክር በሚመለከትም ለ1809 አቅመ ደካማ ዜጎች ነፃ የሕግ ድጋፍ ተደርጓል ።

የሰብዓዊ መብት ጉዳዮችን በተመለከተም በበጀት አመቱ ከተከናወኑ ተግባራት ውስጥ በ25 ማረሚያ ቤቶች በመገኘት 38 ሺ በላይ ታራሚዎችን አያያዝ የተጎበኘ ሲሆን የሕግ ተገዥነት ማሳደግ በሚመለከት 9 የፌደራል ተቋማት ላይ ክትትል ተደርጓል።

ነፃ የሕግ ድጋፍን በሚመለከት ጠበቃ ቀጥረው መከራከር ለማይችሉ ዜጎች 913 ነፃ አገልግሎት ተሰጥቷል። የፍትሕ አገልግሎት አሰጣጥን ማሳደግ በተመለከተ በአመቱ ለ518 ጠበቆች ፈቃድ የተሰጠ ሲሆን በጠበቆች ቦርድ ፅ/ቤትም በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል።

በአጠቃላይ በዘርፋ ስር ባሉ የአሰተዳደር ችሎትና ሌሎች የስራ ክፍሎች በርካታ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን ከእነዚህ ስራዎችም በብቃት መምራት፣ በትብብር መሥራትና ትጋት የተወሰዱ ትምህርቶች መሆናቸውን ወ/ሮ ትብለጥ በሪፓርት ማጠቃለያቸው አውስተዋል።

ቀጥሎም የዘርፋ የሱፐር ቪዥን ግኝቶችን በመንግሥት ሕግ እና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስተር ዲኤታ አማካሪ በሆኑት በወ/ሪት ሀወኒ ታደሰ የ2016 የበጀት ዓመት የዘርፉ እቅድ ደግሞ በፍትሐብሔር ፍትሕ አስተዳደር ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል በአቶ ንጉሴ ትዛዙ አማካኝነት በተከታታያ ቀርቧል።

በቀረበው ሪፓርትና እቅድ ላይ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ፈቃዱ ፀጋና በመንግሥት ሕግና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አለምአንተ አግደው አወያይነት ውይይት ተካሂዶበታል።

Tagged Under: Access to Justice Budget Execution criminal Criminal Justice democratic directives drafting enforcement ethiopian federal democratic republic federal Human Trafficking International Arbitration Justice law Law Enforcement legal Legal Aid Legal drafting Pardon Parole Police prison prison reform pro bono legal services proclamations reform regulations republic Rule of Law Security
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች