አስተዳደራዊ ፍትህን ለማስፈን የተደነገገውን የፌዴራል አስተዳደር ሥነ-ሥርአት አዋጅ በተሻለ ለማስተግበር እንዲረዳ ታስቦ የተጀመረው የስልጠና መርሀ-ግብር መሰጠቱ ቀጥሏል

Training Program Launched to Better Implement the Federal Administrative Procedure Proclamation Enacted to Ensure Administrative Justice Continues

አስተዳደር ሥነ-ሥርአት አዋጅን በተሻለ ለማስተግበር የሚያስችል አቅምን ከማጎልበት አንጻር በተጀመረው የሕግ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና መርሀ ግብር መሠረት ለፌዴራል ተቋማት ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ሥልጠና እየተሰጠ ስለመሆኑ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

መርሀ ግብሩ ቀጥሎ 34 የሚሆኑ ለባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እና ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተጠሪ ለሆኑት የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ፣ የኢትዮጵያ ጸረ አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን፣ የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻህፍት አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራረሮች የአስተዳደር ሥነ ሥርዓት አዋጁን አስመልክቶ ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡

ሥልጠናውን የሰጡት በፍትሕ ሚኒስቴር የመንግሥት ሕግ እና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ ወ/ት ሀወኒ ታደሰ በመመሪያ አወጣጥ ሂደት፣ ስለ አስተዳደራዊ ውሳኔ አሰጣጥ፣ በውሳኔ ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎች ስለሚስተናገዱበት አግባብ እንዲሁም በአዋጁ የተቀመጡትን ግዴታዎች አለማክበር የሚያሰከትለውን ውጤትና የፍርድ ቤቶች ኃላፊነትና ሥልጣንን አስመልክተው ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

አማካሪዋ በማብራሪያቸው አስተዳደራዊ ፍትሕ አንደ ሌሎች የፍትሕ አይነቶች ሁሉ ዜጎች ሊኖራቸው የሚገባ መብት እንደሆነ እና የአዋጁ አጠቃላይ ፋይዳ አስተዳደራዊ ፍትሕ በማስፈን በዜጎችና በመንግሥት መካከል በሕግ ላይ የተመሰረተ ተገማች የሆነ ግንኙነት በመፍጠር የህገ-መንግሥት የበላይነት የተረጋገጠበትና መልካም የመንግሥት አስተዳደር መፍጠር መሆኑን በሰፊው አብራርተዋል፡፡

በቀረበው ገለጻ ላይ ተመርኩዘው ተሳታፈዎች ባነሷቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን የተቋማቱ አመራሮች በሰጡት አስተያየት ለአዋጁ ተፈጻሚነት የበኩላቸውን ለመወጣት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል፡፡

በንቅናቄው ቀጣይ ቀናት በርካታ የመንግሥት ተቋማት ሥልጠናውን እንዲወስዱ እንደሚደረግ ተጠቁሟል፡፡

Tagged Under: Accountability administrative administrative decision-making administrative justice Awareness building capacity Capacity Building federal Federal Administrative Procedure Proclamation Good Governance Government Government Officials judicial review Justice legal Legal Awareness Legal Compliance ministry of culture and sports national archives and library agency national theatre procedure proclamation program Rule of Law Training training program
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች