የአስተዳደር ስነ ስርዓት አዋጅን በክልሎች የማርቀቅ እና የማፀደቅ ሂደት ላይ የሚመክር ሀገራዊ የውይይት መድረክ ተካሄደ

National Discussion Forum Held to Advise on the Process of Drafting and Approving Administrative Procedure Proclamation in Regions

በፍትሕ ሚኒስቴር የፌደራል ህጎች ተፈፃሚነት መከታተያ ዳይሬክቶሬት ከGIZ ጋር በመተባበር በክልሎች የአስተዳደር ሥነ ሥርዓት አዋጅን የማርቀቅ እና የማፀደቅ ሂደት ላይ የሚመክር የክልል ሕዝብ ተወካየች ም\ቤት አፈጉባኤ፣ የሕግና ፍትሕ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች፣ የክልል ፍትሕ ቢሮ ኃላፊዎች፣ የአጋር ድርጅቶች ተወካዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ሀገራዊ የውይይት መድረክ መጋቢት 19 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ አካሂዷል፡፡

ሀገራዊ የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ\ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በሕግ እና ፍትሕ ማሻሻያ ስርዓት ከፀደቁ አዋጆች ውስጥ የአስተዳደር ሥነ ሥርዓት አዋጅ ትልቅ ፋይዳ ያለውና በዘላቂነት መሠረታዊ ለውጦች ያመጣሉ ተብለው ከሚታሰቡት ውስጥ አንዱና ዋነኛው አዋጅ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ሚኒስትሩ አክለውም የአስተዳደር ሥነ ሥርዓት አዋጁ በፌደራል ብቻ መውጣቱ ስራውን ቁንፅል እንደሚያደርገው በመግለፅ አብዛኛው ዜጋ ያለውና አገልግሎት የሚያገኘው በክልሎች በመሆኑ ተመሳሳይ የሕግ ማዕቀፍ ያለው የአስተዳደር ሥነ ሥርዓት አዋጅ በክልሎች መፅደቅ ጠቀሜታው እጅግ ከፍተኛ መሆኑንና በየተቋማት የሚቀርቡ ቅሬታዎችን እንደሚቀንስ ገልፀዋል፡፡

በፍትሕ ሚኒስቴር የፌደራል ህጎች ተፈፃሚነት መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሀወኒ ታደሰ በበኩላቸው የአስተዳደር ሥነ ሥርዓት ህጉ በፌደራል ደረጃ መውጣቱን ተከትሎ በክልሎችም ለማርቀቅ እና ለማፀደቅ በሚያግዝ መልኩ ምክክር ለማድረግ ያለመ መድረክ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

አስተዳደር ስነ-ስርዓት ሕግ በክልሎች ፀድቆ ወጥ የሆነ የመንግሥት አስተዳደር ስርዓት እንዲኖር ለማስቻል ቅድሚያ ሰጥተው የሚደግፉት መሆኑን የገለፁት ደግሞ የGIZ ተወካይ ሚ/ር ክርስቲያን ፒተርስ ሲሆኑ የጀርመን መንግሥት ከኢትዮጲያ የፍትሕ ዘርፍ ጋር በርካታ ስራዎችን በመሥራት የቆየ ግንኙነት ያለው መሆኑን ጠቁመው የመልካም አስተዳደር ግንባታ ላይ በተለያየ መልኩ ድጋፍ እያረገ መሆኑን አክለው ገልፀዋል፡፡

የአስተዳደር ስነ-ስርዓት ሕግ አጠቃላይ ዳሰሳ እና ጠቀሜታ በዶ\ር መሀሪ ረዳኢ የቀረበ ሲሆን የአስተዳደር ሕግ የመንግሥት ሕግ ዘርፍ ሲሆን የመንግሥት አስፈፃሚ አካላት አመሰራረት ፣ አደረጃጀት፣ ሥልጣንና ተግባር ሲያከናውኑ ሊከተሏቸው የሚገቡ መርሆዎችንና ስነ-ስርዓቶችን የሚደነግግ ሕግና አስተዳደራዊ ተግባራቱ ቁጥጥር ክለሳና መፍትሄ የሚሰጥበትን ስርዓት የሚያመላክት ሕግ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

የአስተዳደር ስነ-ስርዓት ሕግ አጠቃላይ ዳሰሳ እና ጠቀሜታ መቅረቡን ተከትሎ የፌደራል አስተዳደር ስነ- ስርዓት አዋጅ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድርና በፌደራል ተቋማት ያለው አተገባበር ሁኔታ በዳይሬክተሯ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በተሳታፊዎች በተነሱ ሀሳብ፣ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያዎች ተሰጥቷል፡፡

ቀጥሎም የአስተዳደር ስነ- ስርዓት በማፀደቅ ሂደት ክልሎች የሚገኙበትን ደረጃ እና ልምድ ያጋሩ ሲሆን የምክክር መድረኩም የድጋፍ ሁኔታዎችን በመለየት እና የወደፊት የስራ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቋል፡፡

Tagged Under: administrative Administrative Law administrative procedure proclamation Capacity Building drafting legislation federal Federal Government framework germany GIZ good Good Governance governance Government governments legal legal framework Legal Reform legislation National national discussion forum procedure proclamation Public Administration Regional Regional Governments Stakeholder Consultation
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች