በፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኤርምያስ የማነብርሀን የተመራው ልዑክ ቡድን የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት እና የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ የክልል እና የተማ አስተዳዳር ፍትሕ ቢሮዎችን፣ የጥናትና ምርምር እና የሲቪል ሶሳይቲ ተወካዮችን ያካተተ ሲሆን፣ የልምድ ልውውጥ ፕሮግራሙም ለአንድ ሳምንት የቆየ እንደነበር ተገልፆል፡፡
ቡድኑ በዋናነት የአስተዳዳር ፍትሕን ለማስፈን ዋነኛ የሕግ መሰረት በሆነው የአስተዳዳር ሥነ-ስርዓት ሕግ አፈፃፀም ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ ወጥ የሆነ የአስተዳዳር ሥነ-ስርዓት ሕግ በፌደራል የመንግሥት ስርዓት ውስጥ ስለሚፈፀምበት መንገድ፣ የአስተዳዳር ፍርድ ቤቶች ስላላቸው ሚና እንዲሁም ለአስተዳዳር ፍትሕ መስፈን የመንግሥት ሰራተኛው ስለሚወስደው ድርሻ የሁለቱን ሀገራት ልምዶችን በሰፊው ማጋራት ተችሏል፡፡
ልዑክ ቡድኑ የጀርመን አስተዳዳር ፍርድ ቤቶችን፣ የፍትሕ ሚኒስቴር፣ የጀርመን የሀገር ውስጥ ሚኒስቴርን፣ የሰው ሀብት አስተዳዳር ተቋም፣ የመንግሥት አስተዳዳር ማሰልጠኛ ተቋማትን፣ የከተማ መስተዳዳርን እንዲሁም የጠበቆች ባር ማህበር ላይ በመገኘት ከተቋማት መሪዎች ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ መክሯል፡፡
ኢትዮጲያ የፌደራል አስተዳዳር ሥነ-ስርዓት ሕግ አውጥታ መተግበር ከጀመረች ጥቂት አመታታ የተቆጠሩ ሲሆን፣ ክልሎች የራሳቸውን የአስተዳዳር ሥነ-ስርዓት ሕግ እንዲያወጡ በፍትሕ ሚኒስቴር በተደረገ ድጋፍ ሕጉን አውጥተው መተግበር የጀመሩ ክልሎች ቁጥር 9 መድረሱ ይታወሳል፡፡
በቀጣይ የአስተዳዳር ፍትሕን ለማሻሻል የሚረዱ የሕግ፣ የፍትሕ እና የሲቪል ሰርቫንት የማሻሻያ ጉዳዮች የትብብርና የድጋፍ ጉዳዮችን በመለየት አብሮ ለመስራት መግባባት ላይ ለመድረስ ተችሏል፡፡ ይህም በቀሪ ክልሎች ህጉ እንዲወጣ የሚደረገውን ድጋፍ አጠናክሮ ማስቀጠልን ጨምሮ በክልሎች የአስተዳደር ሥነ- ስርዓት ትግበራን በተለያዩ መንገዶች መደገፍን ያካትታል፡፡