የአስፈጻሚ ተቋማት የፌዴራል አስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅን በተሻለ በመፈጸም የሕዝቡን አስተዳደራዊ ፍትሕ ጥያቄ በሚመልስ መልኩ መፈጸም እንዲችሉ በአዋጁ ዓላማ እና ይዘት ዙሪያ ለተለያዩ ተቋማት አመራሮች ሥልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል።
በዚህም መሠረት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ቀጥሎ ለትምህርት ሚኒስቴር እና ለሚኒስቴሩ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት አመራሮች የፌዴራል አስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጁን አስመልክቶ ሥልጠና ተሰጥቷል።
ሥልጠናውን በፍትሕ ሚኒስቴር የሕጓች ተፈጻሚነት መከታተያ ዳይሬክተር ወ/ሮ ትብለጥ ቡሽራ እና የመንግሥት ሕግ እና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ ወ/ት ሀወኒ ታደሠ ሰጥተዋል።