ሀወኒ ታደሰ

ዳይሬክተር
ከጥቅምት 2016 ዓ.ም. ጀምሮ

ሀወኒ ታደሰ ከጥቅምት 2016 ዓ.ም ጀምሮ የፌደራል ሕጎች ተፈጻሚነት መከታተያ የሥራ ክፍልን በመምራት ላይ ይገኛሉ። በኢትዮጵያ በሚገኙ በሁሉም የመንግሥት ተቋማት የፌዴራል ሕጎች ውጤታማ እና ወጥነት ባለው መልኩ ተፈፃሚ መሆናቸውን በማረጋገጥ እንዲሁም አስፈፃሚ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሥራቸውን በሕግ መሰረት ማከናወናቸውን በማረጋገጥ ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። በእርሳቸው አመራር የሥራ ክፍሉ ጠንካራ የክትትል ዘዴዎችን በማዘጋጀትና መተግበሩን በበላይነት በመከታተል፣ የህግ ኦዲት በማድረግ፣ የፌዴራል አስፈጻሚ አካላትን በመከታተል የሚስተዋሉ የአሰራር ክፍተቶች ቅንጅቶችን በመለየት በመፍታት እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የማስተካከያ እርምጃዎች መወሰዱን እንዲረጋገጥ አስችላለች፡፡ ከዚህ ባለፈም የህግ የበላይነትን እና የመልካም አስተዳደር እንዲጠናከር በስልጠና መርሃ ግብሮች፣ በአገራዊ ሁነቶች እና ማነቃቂያ ስራዎችን በመስራት ላይ ትገኛለች።  ሀወኒ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ተግባር ለመደገፍ ከአጋር እና ባለድርሻ አካላት በተሳካ ሁኔታ በመቀናጀት የህግ ተገዢነትን ለማጠናከር እና ለዜጎች የፍትህ ተደራሽነት የላቀ አስተዋጽኦ በማበርከት ስኬታማ ናት፡፡

አሁን ካለችበት የአመራርነት ተልዕኮ አስቀድሞ በተለያዩ ደረጃዎች ስታገለግል የቆየች ሲሆን በዋናነት  ከፍተኛ አመራሮችን በማማከር፣ የተወሳሰቡ ወንጀሎችን ለፍርድ በማቅረብ እና የሀገራዊ የህግ እና የፖሊሲ ማሻሻያ ስራዎች ላይ ሰርታለች፡፡ ከ1o አመት በላይ ያካበተችውን ልምድ በመጠቀም ውጤታማ የሆነ የህጎች ተፈፃሚነት እና አስፈፃሚ የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች ላይ ክትትል በማድረግ በኢትዮጵያ የፍትህ፣ የመልካም አስተዳዳር እና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ ሀላፊነቷን ለመወጣት ዝግጁ ናት:: ስራዋ በኢትዮጵያ ፍትህ እና የህግ የበላይነትን ለማስፈን ያላትን ጥልቅ ቁርጠኝነት ያለማቋረጥ ያሳያል።

የትምህርት ዳራ

  • የጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ የህግ ዲግሪ
  • የኢትዮጰያ ስነ-መኮት ድህረ ምርቃ ት/ቤት፣ አመራር እና አስተዳደር ማስተርስ ዲግሪ

ዜና