የሕግ ጉዳዮች ዓለም ዓቀፍ ትብብር ዳይሬክቶሬት የፍትሕ ሚኒስቴር በሕግና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ሥር የተደራጀ የስራ ክፍል ነው፡፡ በሥራ ክፍሉ ከሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ውስጥ በወንጀል እና በፍትሐብሔር ጉዳዮች ዓለም ዓቀፍ ግንኙነትና ትብብር ማድረግ፣ አገራችን ያፀደቀቻቸውን ወይም የተቀበለቻቸውን ዓለም ዓቀፍ እና አህጉራዊ የሰብዓዊ መብቶች ስምምነቶች በተመለከተ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የአፈጻፀም ሪፖርት አዘጋጅቶ ማቅረብ፣ ከተለያዩ አካላት ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ወይም ጉዳዮች ምላሽ መስጠት፣ በሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን መድረኮች ላይ በሕግ ጉዳዮች ዙሪያ ተሳትፎ ማድረግ፤ በወንጀልና በፍትሐብሔር ጉዳዮች ዓለም ዓቀፍ ትብብር ረቂቅ ስምምነቶችን የማዘጋጀት፣ አስተያየት የመስጠት፣ የመደራደር እና ተያያዥ ሥራዎች ይገኙበታል፡፡
