ኢትዮጵያና አየርላንድ በፍልሰት እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አደረጉ

Ethiopia, Ireland Discuss Migration and Related Matters

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የመንግስት ህግ እና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ በላይሁን ይርጋ ከአየርላንድ ፍትሕ ሚኒስቴር የፍልሰት ጉዳዮች ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ኮልም ብሮፒ (H.E. Colm Brophy) ጋር በፍልሰትና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ወቅት የአየርላንዱ ክቡር ሚኒስትር ዲኤታ ከረጅም ዓመታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው በተለይም በእነዚህ ዓመታት ውስጥ በአዲስ አበባ የተመለከቷቸው ዘርፈ-ብዙ ለውጦች እንዳስገረሟቸው ተናግረዋል።

የሁለቱ ወገኖች ውይይት በዋናነት በአሁኑ ወቅት ዓለም አቀፋዊ አጀንዳ በሆነው የፍልሰት ጉዳይ ላይ ያተኮረ ሲሆን በተለይም በፍልሰተኞች ሰብዓዊ መብት አያያዝና ጥበቃ ዙሪያ ሰፊ ምክክር ተደርጓል። የአየርላንድ መንግስት በኢትዮጵያ የሚገኙ የሱዳን ፍልሰተኞችን የቋንቋና የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት ወደ አየርላንድ ወስዶ በማስፈር አዲስ ሕይወት እንዲመሰርቱ ለማድረግ መዘጋጀቱን የገለጹት ክቡር ሚኒስትር ዲኤታው፣ ለዚህም ተግባራዊነት የኢትዮጵያን መንግስት ድጋፍ እንደሚፈልጉ ጠቁመዋል።

ክቡር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በላይሁን ይርጋ በበኩላቸው፤ አገሪቱ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ለፍልሰት አስተዳደር ትልቅ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን አብራርተዋል። ከእነዚህም መካከል በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የሚመራ ምክር ቤት ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱን፣ የተለያዩ የፍልሰት ቡድኖች ተዋቅረው በፍትሕ ሚኒስቴር አስተባባሪነት እየሰሩ መሆኑን እና ጉዳዩ የአንድ አገር ብቻ ባለመሆኑ ከበርካታ አገራት ጋር የትብብር ስምምነቶች መፈረማቸውን አስገንዝበዋል።

አክለውም ኢትዮጵያ በፍልሰተኞች ረገድ መነሻ፣ መተላለፊያና መዳረሻ አገር እንደመሆኗ መጠን፣ የአየርላንድ መንግስት ያቀረበውን ጥያቄ ስኬታማ ለማድረግ የኢትዮጵያ መንግስት የበኩሉን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል። በመጨረሻም፣ የእለቱ ውይይት በሁለቱ አገራት መካከል ጠንካራ ግንኙነት ለመፍጠርና በቀጣይም በፍልሰትና በሌሎች ተያያዥ የፍትሕ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት መልካም መሰረት የሚጥል መሆኑን በመግለጽ፣ ለአየርላንድ መንግስት ለሰጠው ትኩረት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Tagged Under: adama science and technology university Addis Ababa Science and Technology University addis ababa water and sewerage authority african charter on human and peoples’ rights african charter on the rights and welfare of the child african commission on human and peoples' rights agricultural land and cultural rights and healthcare administration and healthcare administration and control authority and medium enterprises (msmes) and peoples' region and peoples' region (snnpr) arra (agency for refugees and returnees affairs) article 55(1) and (11) article 55(1) and (12) arts and culture Business and Human Rights central bank of ethiopia ethiopia revenue and customs authority ireland land matters medicine and healthcare administration and control authority medicine and healthcare administration and control proclamation no. 661/2009 Migration ratio related technical and vocational education and training technical and vocational education and training (tvet)
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች