የፍልሰት አስተዳደር ውጤት ተኮር የእቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምግማ ላይ ያተኮረ ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል

Training on Outcome-Based Migration Management Planning, Monitoring, and Evaluation Underway

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ከአለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት (IOM) ጋር በመተባበር የፍልሰት አስተዳደር ውጤት ተኮር የእቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ላይ ያተኮረ ሥልጠና በሰው መነገድና ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀሎች መከላከልና መቆጣጠር እንዲሁም በአጠቃላይ ከፍልሰት አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ባለድርሻ ለሆኑ የፌዴራልና የክልል ተቋማት ተወካዮዎች ለሦስት ቀን የሚቆይ ሥልጠና በአዳማ ከተማ በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡

የሥልጠና መድረኩን በንግግር የከፈቱት በፍትሕ ሚኒስቴር የብሔራዊ ትብብር ጥምረት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም አያሌው እንዳሉት የፍልሰት ስራ በየተቋማቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ ተካቶ እንዲታቀድ፣ እንዲመዘንና እንዲገመገም ለማሰቻል ያለመ መሆኑን ገልጸው ስራው እንደኮሚቴ የሚሰራ ሳይሆን ወደ ተቋም ወርዶ በየተቃማቱ ተቋማዊ እቅድ ውስጥ ተካተው የሚሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ኃላፊው በንግግራቸው ሥልጠናው በሁለት ዙር እየተሠጠ ያለ ሲሆን በመጀመሪያው ዙር የብሔራዊና ክልላዊ የትብብር ጥምረት አባል ተቋማት ተወካዮች (Focal Persons) የተሰጠ መሆኑን አውስተው፤ ዛሬ መሰጠት የተጀመረው ሥልጠና ለትብብር ጥምረቶቹ አባል ተቋማት የእቅድ ዝግጅት፣ ግምገማና ሪፖርት ክፍል የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎችን ክህሎት ለማዳበር ያለመ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ሥልጠናው የአምስት አመቱን የፍልሰት ስትራቴጂክ እቅድ ግምገማ ውጤት ፣የብሔራዊ ትብብር ጥምረት አሠራር የአካታችና የተጠያቂነት ሥርዓት የዳሰሳሰ ጥናት፣ እንዲሁም የብሔራዊና ክልላዊ ትብብር ጥምቶች ተቋማዊ የአቅም ሁኔታ ዳሰሳ ግኝቶችን መነሻ ያደረገ መሆኑን ያወሱት ሀላፊው፣ የፍልሰትን አስተዳደር ስራን ለመሥራት በሕግ ሥልጣን የተሰጣቸው አካላት ስራውን በጎንዮሽ ማየት ሳይሆን የተቋማቸው የስራ አካል አድርገው ይተገብሩታል ወይ የሚለውንም ጉዳይ መነሻ ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አክለውም ይህ ሥልጠና ተተቋማት የፍልሰት ጉዳይን የእቅዳቸው አካል አድርገው ሥራን መሠረት አድርጎ ተጠያቂነትን ለማስፈን እንዲያስችል ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሥልጠናው በፍልሰት ጉዳይ ላይ ብቻ ሳይወሰን ሳይንሳዊ የሆነና ለሁሉም የዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ሥራዎች ለማሻሻል የሚጠቅም ሳይንሳዊ ይዘት ያለው መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

Tagged Under: IOM Collaboration • Migration Management • Stakeholder Training
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች