በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የፍትሕ ሚኒስቴር እና በቱርኪዬ ሪፐብሊክ የፍትሕ ሚኒስቴር መካከል በፍትሕ ነክ ጉዳዮች ጠንካራ ትብብር ስለሚኖርበት ሁኔታ ውይይት ተካሄደ

Discussion Held on Strengthening Bilateral Cooperation in Justice Matters Between Ethiopia and Turkey

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ በላይሁን ይርጋ የተመራ የልዑክ ቡድን በቱርኪዬ – አንካራ በመገኘት ከተለያዩ የመንግሥት የበላይ አመራር እና የስራ ሃላፊዎች ጋር በሕግና በፍትሕ ሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

በዚህም መሠረት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው እና በቱርኪዬ ሪፐብሊክ የፍትሕ ምክትል ሚኒስትር ክቡር ሚ/ር ሁርሺት ይልድሪም (Hurşit YILDIRIM) መካከል በሁለቱ ሀገራት በፍትሕ ዘርፉ ያለው የሁለትዮሽ ግንኙነትና ትብብር በሚጠናከርበት ሁኔታ ዙሪያ ውይይት ጥር 13 ቀን 2017 ተካሄዷል፡፡

በዚህ ወቅት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው እንደገለፁት በኢትዮጵያ እና በቱርኪዬ መካከል ዘመናትን ያስቆጠረ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት መኖሩንና በአሁኑ ወቅት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በኢንቨስትመንት እና በመሳሰሉት ያለው ትብብር እየተጠናከረ መምጣቱን ገልፀው ይህ ግንኙነት በሕግና በፍትሕ ጉዳዮች ጭምር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለማድረግ በኢትዮጵያ በኩል ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩን፣ ይህን ከማሳካት አንጻር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላቸው ስምምነቶች እና መግባቢያ ሰነዶች ባለፉት ሁለት ዓመታት የተፈረሙ ሲሆን በኢትዮጵያ በኩል መጽደቅ የሚገባቸው የሁለትዮሽ ስምምነቶች በሚኒስትሮች ም/ቤት ተቀባይነት አግኝተው በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፀደቁ መሆናቸውን፣ በቱርኪዬ በኩልም በተመሳሳይ ቅድሚያ እና ትኩረት አግኝተው እንዲፀድቁ እና ወደስራ እንዲገቡ እንደሚደረጉ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም በዚሁ ወቅት የሁለቱ ሀገራትን ትኩረትና ትብብር የሚፈልጉ ሌሎች ጉዳዮች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በዚህ ጊዜ የቱርኪዬ የፍትሕ ምክትል ሚኒስትሩ እንደገለፁት ሁለቱ ሀገራት ቀደምት ታሪክ ያላቸው፣ ግንኙነታቸው ረጅም ዘመን ያስቆጠረ መሆኑን አስታውሰው ይህ ግንኙነታቸው በፍትሕ ዘርፍ እንዲጠናከር በትብብር ለመሥራት ያላቸውን ቁርጠኝነት እና በሁለቱ ሀገራት መካከል የተፈረሙት መጽደቅ የሚፈልጉት ስምምነቶች እንዲፀድቁ ለማድረግ አስፈላጊውን ሁሉ በአጭር ጊዜ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም በዚሁ ወቅት ትብብር ከሚደረግባቸው ፍትሕ ነክ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ከምክትል የፍትሕ ሚኒስትሩ ባሻገር ከሌሎች መ/ቤቶች የመጡ የሚመለከታቸው ኃላፊዎች ያላቸውን ሃሳብ ሰጥተዋል፡፡

ከፍትሕ ሚኒስትር ዴኤታው ጋር በመሆን በፍትሕ ሚኒስቴር የፍትሐብሔር ፍትሕ አስተዳደር ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ሄኖክ ተስፋዬ እና በሕግ ጉዳዮች ዓለም አቀፍ ትብብር ዳይሬክተር አቶ የሱፍ ጀማው እንዲሁም በቱርክ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ ም/አምባሳደር ክቡር አቶ ሙሌ ታረቀኝ እና አቶ ይርጋ ተገኝተዋል፡፡

Tagged Under: african charter on the rights and welfare of the child and healthcare administration and control authority bilateral Bilateral Cooperation constitution of the federal democratic republic of ethiopia Convention on the Rights of the Child convention on the rights of the child (crc) Cooperation criminal justice cooperation Discussion ethiopia revenue and customs authority federal institute of justice and law federal justice and law institute government law and justice services sector international criminal justice cooperation Justice justice and democracy affairs justice and law institute Justice For All - PF Ethiopia justice for all prison fellowship ethiopia justice system strengthening key matters operation per ratio strengthening turkey
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች