በአማራ ክልል በሰብዓዊ መብቶች አያያዝ፣ በአገራዊ የሰብዊ መብት ክትትል እና የዓለም ዓቀፍ የሕግ ድንጋጌዎች አተገባበር ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ

A training focused on human rights handling, national human rights monitoring, and the implementation of international legal provisions was given in the Amhara Region

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የሰብዓዊ መብቶች ዳይሬክቶሬት ከተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ጋር በመተባበር በክልሉ ለሚገኙ የፍትሕ ተቋማት እና የሰብዓዊ መብቶች ተቋማት አመራሮች እና ባለሙያዎች በሰብዓዊ መብቶች አያያዝ፣ በአገራዊ የሰብዓዊ መብት ክትትል እና የዓለም ዓቀፍ የሕግ ድንጋጌዎች አተገባበር ላይ ያተኮረ ሥልጠና በአዳማ ከተማ ከመስከረም 20/ 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

የሥልጠናዉ ዋና ዓላማ አጠቃላይ በሰብዓዊ መብቶች በተለይም በጥበቃ ሥር ያሉ እና በፍርድ ቤት ትዕዛዝ የታሰሩ ሰዎች መብት አፈጻጸም መርሆዎች ላይ የሰልጠኞችን ክህሎት ማሳደግ መሆኑም ተመላክል፡፡

በመድረኩ የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶ/ር አያሌው አባተን ጨምሮ ከፌዴራል እና ከክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ከፍትሕ ቢሮ፣ ከፖሊስ ኮሚሽን እና ማረሚያ ቤቶች እንዲሁም ክልሉ ላይ ከሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የተወከሉ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን፣ መሰል ስልጠናዎች ባለፉት ዓመታት የነበሩ ክፍተቶችን በመለየት በቀጣይ ለማሻሻል የሚያስችል ክህሎቶችን ለማዳበር አስተዋጾ እንዳለው ምክትል ኃላፊው ገልጸዋል።

በዚህም ወቅት የፍትሕ ሚኒስቴር የሰብዓዊ መብቶች ክትትል ማኑዋል፣ የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ሪፖርት፣ ምክረ ሃሳቦች እና ሁሉን ዐቀፍ ወቅታዊ ግምገማ ላይ ያተኮሩ ሃሳቦች፣ የተጠርጣሪዎች እና ታራሚዎች መብቶችን የሚደነግጉ ዓለም አቀፍ የህግ ማዕቀፎች፣ እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ዳይሬክቶሬት በክልሉ ከሚገኙ ማረሚያ ቤቶች አንዱ በሆነው የኮምቦልቻ ማረሚያ ቤት ባደረገው ጉብኝት የተስተዋሉ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች እንዲሁም ዐበይት ምክረ ሀሳቦች እና የማስፈጸሚያ ስልቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

ኢትዮጵያ በተቀበለቻቸዉ ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጊዎች አተገባበር ላይ የታዩ ክፍተቶች እና ተግዳሮቶች በሥልጠናዉ ላይ የተወሳ ሲሆን፣ በ2018 በጀት ዓመት እንደ ሀገር የተቀበልናቸዉን ምክረ-ሀሳቦች ለመፈጸም ፍኖተ ካርታ እና የድርጊት መርሀ-ግብር ማዉጣት፣የፌደራል እና የክልል ማረሚያ ቤቶችን መጎብኘት፣ አገራዊ የአፈጻጸም ሪፖርትን አዘጋጅቶ ማቅረብ እና የአገሪቱን የጋራ ዋና ሰነድ(Common Core Document) አሻሽሎ ማቅረብ ዋነኛ የትኩረት አቅጣቻዎች እንደሆኑ ተጠቁሟል፡፡

Tagged Under: Amhara amhara region common document handling human Human Rights human rights monitoring Implementation international judicial legal Legal Provisions monitoring National pro provision provisions region right Rights ring Training un UNDP Use used vision
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች