ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ በሕግና ፍትሕ ጉዳዮች የሁለትዮሽ ትብብር ጉዳዮች ዙሪያ መከሩ

Ethiopia, Nigeria Hold Talks on Bilateral Cooperation in Law and Justice

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሐና አርአያስላሴ በአገራችን የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ከሚገኙት የናይጄሪያ ፌዴሬሽን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና የፍትሕ ሚኒስትር ክቡር ሚ/ር Lateef Olasunkanmi Fagbemi ጋር በሁለቱ አገራት የጋራ ጉዳዮች በተለይም በሕግና ፍትሕ ጉዳዮች የሚደረጉ ትብብሮችን በተመለከተ የጋራ ምክክር ሰኔ 3/2018 ዓ.ም አድርገዋል።

ክቡር ሚኒስትሩ ወደ አዲስ አበባ ሲገቡ ለተደረገላቸዉ ደማቅ አቀባበል እና መስተንግዶ ምስጋናቸውን የገለፁ ሲሆን፣ ሁለቱ አገራት በተለያዩ ዘርፎች አብሮ በመስራት ሂደት ለአመታት የዘለቀ ጠንካራ እና ዉጤታማ ግንኙነት እንዳላቸው አንስተው በተለይም ከፍትሕ ዘርፉ ጋር በተያያዘ በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ በቀጣይ አብረው ለመስራት ውይይቱ ከፍ ያለ ጠቀሜታ እንዳለው አንስተዋል።

በምክክሩም ድርድሩ የተጠናቀቀውና በዛሬው ዕለት ይፈረማል ተብሎ ስለሚጠበቀው ፍርደኞችን የማስተላለፍ ስምምነት እንዲሁም ሌሎች በሂደት ላይ የሚገኙ የሁለትዮሽ ስምምነቶችን በማጠናቀቅ ለፊርማ ዝግጁ ማድረግ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ግንኙነት በማጠናከር ረገድ ስላለው አስተዋፅኦ፤ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በመከላከል ረገድ በሁለቱ አገራት መካከል የሚኖሩ ትብብሮች ለሁለቱም አገራት ስለሚያስገኙት ጠቀሜታ፤ ማረሚያ ቤቶችን በማሻሻል ረገድ በአገራችን በኩል ስለተከናወኑ የሪፎርም ተግባራት እንዲሁም በሁለቱ አገራት መካከል የልምድ ልውውጥ ሊደረግባቸው የሚችሉ ተሞክሮዎችን በተመለከተ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል።

Tagged Under: act bilateral Bilateral Cooperation Charter constitution Cooperation court decree directive federal institute of justice and law federal justice and law institute fundamental law government law and justice services sector Justice justice and law institute law legislation nigeria old operation per Policy proclamation ratio Regulation standing committee on law and justice statute un
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች