
የሱፍ ጀማው ሰይድ በፍትሕ ሚኒስቴር የበሕግ ጉዳዮች ዓለም ዓቀፍ ትብብር ዳይሬክተር በመሆን ከነሐሴ 2007 ዓ.ም ጀምሮ በማገልገል ላይ ይገኛሉ። በዚህ ኃላፊነት ማገልገል ከመጀመራቸው አስቀድሞ የሚኒስትሮች አማካሪ፣ በመመርመርና ውሳኔ ማሰጠት ዋና የሥራ ክፍል፣ በወንጀል ጉዳዮች መምሪያ፣ በፍትሐብሔር ጉዳዮች መምሪያ፣ በአዲስ አበባ የፍትሕ ሚኒስቴር ተጠሪ ጽ/ቤት (ልደታ) በተለያየ የዐቃቤ ሕግነት ደረጃ አግልግሎት ሰጥተዋል፡፡ በተጨማሪም በኢጋድ ፕሮግራም አማካኝነት በኢትዮጵያ መንግስት ተመድቦ በደቡብ ሱዳን ፓርላማ በአማካሪነት ለሁለት ዓመት አገልግሎት ሰጥተዋል፡፡