በዓለማቀፋዊ የሕግ ትብብር ረቂቅ አዋጆች ዙሪያ ዉይይት ተካሄደ

Discussion Held on Draft Proclamations Regarding International Legal Cooperation

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የተመሩለትን ዓለማቀፋዊ የሕግ ትብብር ረቂቅ አዋጆች ዙሪያ ታህሳስ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከአስረጅዎች ጋር ውይይት አድርጓል።

ህዳር 25 ፣2018 ዓ.ም፤ በምክር ቤቱ 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ከሶስት ሃገራት ጋር ከወንጀልና ፍርደኛን የማስተላለፍ ጉዳዮች ላይ የተደረጉ አራት የሁለትዮሽ ስምምነቶች ለቋሚ ኮሚቴው መመራቱ ያታወሳል።

ሥምምነቶቹ ኢትዮጵያ ፍርደኞችን ለማስተላለፍ ከቻይና፣ብራዚል እና ደቡብ አፍሪካ ጋር ያደረገቻቸው ትብብሮችና በተመሣሣይ በኢትዮጵያ እና በቻይና መንግስታት መካከል የተደረገው የወንጀል ጉዳዮች የጋራ የሕግ ትብብር ረቂቅ አዋጆች እንደሆኑ ተገልጿል።

በዉይይቱ ወቅት ረቂቅ አዋጆቹ ፋይዳቸው ወንጀልን ከመከላከል በላይ ነው ያሉት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ዕፀገነት መንግስቱ የሁለትዮሽ ሥምምነቱን የሚፈርሙት ሀገራት የBRICS አባል ሀገራት በመሆናቸው አዋጆቹ ብዙ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ስትራቴጂካዊ የትብብርን የሚያጠናክሩ እንደሆኑ አብራርተዋል።

የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ በላይሁን ይርጋ በበኩላቸው እነዚህ ስምምነቶች ሀገራት በሰጥቶ መቀበል መርህ በሁለቱም ወገን የሀገራቸውን ጥቅም የሚያስከብሩባቸው ስምምነቶች እንደሚሆኑ አመላክተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታዉ አክለዉም የፖለቲካ ወንጀለኞችን አሳልፎ መስጠት ግን ዓለማቀፋዊ ስምምነቶችም እንደማይፈቅዱ ተናግረዉ ከሽብርተኝነት ጋር የተገናኘ ከሆነ ግን በስምምነቶቹ መሠረት ማስተላለፍ እንደሚቻል ገልፀዋል።

በረቂቅ አዋጆቹ ላይ የቋሚ ኮሚቴው አባላትና በም/ቤቱ የህግ ባለሙያዎች ጥያቄና አስተያየቶች ቀርበው ሰፊ ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን በተገኘው ግብዓት መሠረት ማስተካከያ ተደርጎባቸው እንደሚፀድቁ ተጠቁሟል።

ምንጭ፡- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

Tagged Under: act BRICS Cooperation court decree directive Discussion draft Draft proclamation international international legal cooperation judge judicial judiciary law legal Legal Cooperation legislation National operation per Policy pro proclamation proclamations ratio Regulation statute
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች