የፍትሕ ሚኒስቴር ፍልሰትን አስመልክቶ ከተርክዬ ልዑኳን ቡድን ጋር ውይይት አካሄደ

Ministry of Justice Holds Discussion on Migration with Turkish Delegation

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ፍልሰትን አስመልክቶ ከተርክዬ የተለያዩ ተቋማትን ወክለው ከመጡ ልኡኳን ቡድን ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

በውይይት መድረኩም በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ኤርሚስ የማነብርሀን (ዶ/ር) የኢትዮጵያና የተርክዬ መንግስታት ከቀደምት ጀምሮ በማኅበራዊ ፣በኢኮኖሚያዊ እና በባህላዊ ጉዳዮች ጠንካራ ግንኙነት እንዳላቸው ገልፀው ፤በቀጣይ የኢትዮጵያና የተርክዬ መንግሥት ፍልሰትን አስመልክቶ በትብብር እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

በፍትሕ ሚኒስቴር የብሔራዊ ትብብር ጥምረት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም አያሌው በበኩላቸው ለሉዑኳን ቡድኑ የኢትዮጵያና የዓለም ዓቀፍ ፍልሰት ህጎችና ፖሊሲዎችን፣ ፍልሰተኞች በምን ምክንያት እንደሚፈልሱ ፣ፍልሰተኞች በፍልሰት ወቅት ምን ምን ችግሮች እንደሚገጥማቸው፣ ህገወጥ ፍልሰትን ለመከላከል ምን ምን ተግባራት እየተከናወኑ እንደሆነ፣የፍልሰት መነሻና መዳረሻ ሀገራት፣ ፍልሰትን አስመልክቶ እየተሰሩ ስላሉ ጉዳዮች፣ ከሌሎች ተቋማት ጋር ፍልሰትን በተመለከተ ያሉ የጥምር ስራዎች እንዴት እየተሰሩ እንደሆነ እንዲሁም ከፍልሰት ተመላሽ ዜጎችን በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል፡፡

የቀረበውን ገለፃ ተከትሎ ከሉዑኳን ቡድኑ ጥያቄዎች ቀርበው በአቶ አብረሃም በኩል ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

Tagged Under: bilateral Bilateral Cooperation Cooperation cross-border cross-border migration delegation diaspora diplomatic diplomatic relations Government Government Delegation human Human Trafficking international international migration law irregular Irregular migration law Migration Migration Policy national cooperation Policy reform Refugees relations remittances return return migration trafficking turkey
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች