የሕግ ጥናት፣ ማርቀቅና ማጠቃለል ዳይሬክቶሬት ጀነራል በመንግሥት ሕግ እና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ስር የሚገኝ የሥራ ክፍል ሲሆን የፌዴራል መንግስቱን ሕጎች የማርቀቅ፣ የማጠቃለል፣ የሕግ ጥናቶችን የማከናወን፣ በሌሎች ተቋማት የተረቀቁ አዋጆች ወይም ደንቦች ከመጽደቃቸው አስቀድሞ ከሕጋዊነት እና ከሕግ ማርቀቅ ቴክኒክ ጋር በተያያዘ የማረም፣ ሕግን የተመለከተ ጥያቄ ሲኖር ለመንግሥት ተቋማት የሕግ ምክር የመስጠት፣ የፌዴራል አስፈጻሚ አካላት የሚያወጧቸው መመሪያዎች የፌዴራል የአስተዳደር ሥነ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 ያስቀመተውን የመመሪያ አወጣጥ ሥርዓት የተከተለ መሆኑን የማረጋገጥ እና በአግባቡ የተዘጋጁ መመሪያዎችን በመመዝገብ ቁጥር በመስጠት ለሕዝብ ተደራሽ እንዲሆኑ ማስቻል ከተጣሉበት ኃላፊነቶቹ መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
