በህግ ማርቀቅ ሂደት የህዝብና የባለ ድርሻ አካላት ተሳትፎ ረቂቅ ማንዋል ተዘጋጅቶ ውይይት ተደረገበት

Draft Manual on Public and Stakeholder Participation in the Law Drafting Process Discussed

በሕግ ማርቀቅ ሂደት የሕዝብና የባለ ድርሻ አካላት ተሳትፎን የሚመለከት ረቂቅ ማንዋል ተዘጋጅቶ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የሕግ ባለሙያዎች በተገኙበት በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ውይይት ተደርጎበታል።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር በአዋጅ ከተሰጡት ተግባርና ሀላፊነቶች አንዱበአገሪቱ የሚወጡ ህጓችን ከረቂቅ ጀምሮ እስከ ትግበራው መከታተል ሲሆን በዚሁ መሠረት በሚረቀቁ ህጎች የሕዝብና የባለድርሻ አካላት ምክክር መካሄዱን የማረጋገጥ ሀላፊነቱን ለመወጣት የሚያስችለው ማንዋል አዘጋጅቷል።

በፍትሕ ሚኒስቴር ሕግ ጥናት ማርቀቅና ማጠቃለል ዳይሬክተር ጀነራል አቶ አዲስ ጌትነት ተ እንዳሉት የሚረቀቁ ህጓችን አስመልክቶ የሚካሄዱ የሕዝብ ተሳትፎዎች ወጥነት የሌለውና በተገቢው መልኩ ተሳትፎን ያላረጋገጠ ከዛም አልፎ ቅሬታ የሚቀርብበት ጉዳይ መሆኑን ገልፀው እነዚህንና መሰል ችግሮችን በመቅረፍ የሚወጡ ህጎችን ጥራት ለማረጋገጥ እንዲያስችል ለማድረግ የሕዝብና የባለ ድርሻ አካላት ተሳትፎ የሚመራበት ማንዋል በጂ.አይ.ዜድ እና ከአውሮፓ ህብረት ፕሮጀክት ጋር በመተባበር መዘጋጀቱን አዉስተዋል።

ቀጥሎም ማንዋሉን ያዘጋጁት ዶክተር ውብሸት ሽፈራው (አማካሪ) ለውይይቱ ሳታፊዎች ማንዋሉን አቅርበዋል።

ማንዋሉ ሲዘጋጅ አሁን እየተሰራባቸው ያሉ ስርአቶችና የአፍሪካና የአውሮፓ አገራት ልምዶች ዳሰሳ መደረጉ የተገለፀ ሲሆን ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ ህጎችና ክፍተቶቻቸው፣የሕዝብ ተሳትፎ ምንነት፣ የሕዝብን ተሳትፎ ለማረጋገጥ ስለሚከናወኑ ቅድመ ሁኔታዎች፣ተግባራዊ የሚደረግበት መንገድ የሚሉና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዬችም በማንዋሉ ተካተዋል ።

የሕግ ጥራትን ለመጨመር፣ የሚወጡ ህጎችን ተቀባይነት ለመጨመር፣ በመንግሥትና በሕዝብ መካከል መተማመን እንዲጨምር ለማድረግና ፣ ዲሞክራሲ ስር እንዲሰድ ማድረግን ዓላማ አድርጎ ማንዋሉ መዘጋጀቱ ተገልፆል።

ማንዋሉ በሁሉም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ተግባራዊ እንደሚሆንና ፍትሕ ሚኒስቴርም ተቋማቱ የሚያዘጋጇቸው ህጎች በዚህ ማንዋል ያሉ ሂደቶችን አልፈው የተዘጋጁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የሚረዳው ጠቃሚ መመሪያ ሆኖ እንደሚያገለግልም ተጠቁሟል።

በመጨረሻም በቀረበው ረቂቅ ማንዋል ላይ ከተሳታፊወች ግብአት የሚሆኑ ሀሳብ አስተያየቶች ተሰጥቶበት ውይይቱ ተጠናቋል።

Tagged Under: citizen engagement • Civil Society • Democracy • democratic • drafting • engagement • eu project • FDRE • federal • federal democratic republic of ethiopia (fdre) • GIZ • Good Governance • law • Law Drafting • legal • legal quality • Legal Reform • legislative • legislative process • manual • participation • Policy Development • process • public • Public participation • quality • republic • Rule of Law • stakeholder • Stakeholder Engagement
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች