ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የፋይናንስ አገልግሎት መድብልን ለማዘጋጀት በተደረገ የመነሻ ጥናት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ

Ministry Holds Stakeholder Discussion on Initial Study for Drafting Financial Services Code

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ዘመናዊ የሆነ የፋይናንስ አገልግሎት መድብል ለማዘጋጀት በተደረገ የመነሻ ጥናት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ፡፡

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በፍትሕ ሚኒስቴር የሕግ ጥናት፣ማርቀቅና ማጠቃለል ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አዲስ ጌትነት እንደተናገሩት የንግድ ህጉ በሚሻሻልበት ጊዜ የመድብሉ መጽሀፍ ሶስት እና አራት ማለትም የባንክ ስራና የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶችን እና መድህንን የሚመለከተው የመጽሀፉ ክፍል ካለው ባህሪ አኳያ እራሱን ችሎ የፋይናንስ አገልግሎት መድብል/ኮድ/financial service code/ በሚል እንዲወጣ ማድረግ በማስፈለጉ የፋይናንስ አገልግሎት መድብ የጥናትና አርቃቂ ቡድን ተቋቁሞ ስራዎች ተጀምረው ነበር፡፡

የጥናት እና አርቃቂ ቡድኑ ከፍትሕ ሚኒስቴር፣ ከብሔራዊ ባንክ፣ ከመድህን ሰጪ ድርጅቶች፣ ከባንክ እና ኢንሹራንስ ማህበራት፣ ከዩኒቨርስቲ መምህራን፣ በግል ከሚሰሩ በዘርፉ ሙያ ያላቸው ግለሰቦች ተወጣጥቶ ተቋቁሞ ለስራው አመቺነት የባንክ ስራ እና የኢንሹራንስ ቡድን በሚል በሁለት ቡድን ስራዎችን ሲሰራ ቆይቶ የመነሻ ጥናቱ ተጠናቆ መድብሉን የማርቀቅ ስራው መጀመሩን አቶ አዲስ ገልጸዋል።

ዳይሬክተር ጀነራሉ አክለውም መነሻ ጥናቱ በአገራችን በዘርፉ ያሉ የሕግ ማዕቀፎችን፣ የገበያ ክፍተቱን እና የውጭ ተሞክሮዎችን በመዳሰስ የተሰራ መሆኑን ገልጸው የፋይናንስ ዘርፉን በአግባቡ መምራትና ማስተናገድ የሚችል ዘመናዊ ሕግ ለማዘጋጀት በመነሻ ጥናቱ ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ማድረግና ግብዓት መሰብሰብ አስፈላጊ በመሆኑ የምክክር መድረኩ መዘጋጀቱን አንስተዋል፡፡

በዕለቱ የመነሻ ጥናቱ ግኝቶች በጥናትና አርቃቂ ቡድኑ ለመድረኩ ተሳታፊዎች የቀረቡ ሲሆን ለመድብሉ ዝግጅት ወሳኝ የሆኑ የተለያዩ ሀሳብና አስተያየቶችም በመድረኩ ተሳታፊዎች ተነስተዋል፡፡

በመድረኩ ላይ ከአለም ባንክ፣ከብሔራዊ ባንክ፣ከባንኮች ማህበር፣ከፍትሕ ሚኒስቴርና ከሌሎች በዘርፉ ከተሰማሩ አካላት የተውጣጡ ተወካዮች ተሳትፈውበታል፡፡

Tagged Under: bank Banking banking law code code of conduct Consultation drafting drafting legislation financial financial regulation financial sector reform Financial Services financial services code Insurance insurance law international best practices law legal framework legal research National national bank of ethiopia reform Regulation regulatory reform sector Services stakeholder Stakeholder Consultation World Bank
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች

No data was found