የህብረተሰቡን ፍትህ የማግኘት መብት ለማረጋገጥ ነፃ የህግ ድጋፍ አገልግሎት የሚኖረው ሚና የጎላ መሆኑ ተጠቆመ

The Crucial Role of Free Legal Aid Services in Ensuring Access to Justice

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር እያዘጋጀ ባለው ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ረቂቅ አዋጅ ላይ የተቋሙ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ውይይት አካሄዱ።

ተቋሙ በ2017 ዓ.ም ሊተገብራቸው ካቀዳቸው ዋና ዋና ስራዎች መካከል አንዱ ለነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት የሕግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት መሆኑን የገለፁት የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ በላይሁን ይርጋ ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት እስካሁን አጠቃላይ አገልግሎቱን የሚመለከቱ ዝርዝር ጉዳዮች የተካተቱበት የሕግ ማዕቀፍ ሥርዓት ባለመኖሩ ስራው በተበታተነ መንገድ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።

ከነዚህና መሰል ክፍተቶች በመነሳት እና በተጨማሪም የሌሎች አገራት ተሞክሮ እንደሚያሳየው ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት በዋናነት የመንግሥት ስራ መሆኑን መነሻ በማድረግ ስራውንም ሰብሰብ በማድረግ አገልግሎቱ በሕግና ሥርዓት እንዲመራ ለማድረግ ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

አገልግሎቱን ወደ ማህበረሰቡ በማድረስ ማግኘት ያለበትን አገልግሎት እንዲያገኝ ብሎም ፍትሕ የማግኘት መብቱን ለማረጋገጥ የአዋጁ ሚና የጎላ መሆኑን ክቡር ሚኒስትር ዲኤታው አክለው ጠቁመዋል፡፡

ቀጥሎም የተቋሙ የሕግ ጥናት ማርቀቅና ማጠቃለል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ አዲስ ጌትነት የረቂቁን መነሻ ሁኔታዎች፣ጠቅላላ ድንጋጌዎች፣የአገልግሎት አይነት፣አገልግሎት ሰጭዎችና ተጠቃሚዎች፣የፍትሕ ሚኒስቴርና የክልል ፍትሕ ቢሮዎች ተግባርና ኃላፊነት፣የዲስፕሊን ጥፋቶችና ቅጣት፣ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ፈንድ በሚሉ የረቂቁ ዋና ዋ ይዘቶች ላይ ተመርኩዘው የነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ረቂቅ አዋጅ አጠቃላይ ይዘትን አቅርበው ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተውባቸዋል።

በመጨረሻም በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተሳታፊዎች ሀሳብ አሰተያየቶች ለአርቃቂ ቡድኑ ቀርበው ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጎበት የእለቱ መድረክ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ በውይይት በመድረኩ የተነሱ ሃሳቦች እንደሚያመላክቱት ረቂቅ አዋጁ በአጠቃይ ሰብዓዊ መብቶች የበለጠ እንዲዳብሩ ለማድረግ እና የዜጎች ማኅበራዊ ፍትሕ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የኢኮኖሚ አቅምንና የተለያዩ ማኅበራዊ ምክንያቶችን መነሻ መሠረት አድርጎ የሚፈጠር የፍትሕ መጓደልን ለመከላከል የሚኖረው ሚና የጎላ መሆኑ ተገልፆል።

Tagged Under: Access to Justice • Free Legal Aid • Human Rights
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች