ፍትሕ ሚኒስቴር የ2016 በጀት ዓመት እቅድ 6 ወራት አፈፃፀሙን ገመገመ

Ministry of Justice Reviews Six-Month Performance of 2016 Budget Year Plan

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የ2016 በጀት ዓመት እቅድ 6 ወራት አፈፃፀሙን የተቋሙ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም ሰራተኞች በተገኙበት የካቲት 08 ቀን 2016 ዓ.ም ገምግሟል፡፡

የተቋሙን የ6 ወር አፈፃፀም ሪፖርት የስትራቴጂክ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ መንግስቴ ያቀረቡ ሲሆን በሪፖርቱም የክርክር መዝገቦች (በፍትሕ ሚኒስቴር 24,883 እና በክልሎች ፍትሕ ቢሮ 65,163) በአጠቃላይ 92,011 የክስ መዝገቦች ክርክር ተደረጎባቸው 43,206 መዝገቦች ላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ የተሰጠ ሲሆን 41,376 መዝገቦች የቅጣት ውሳኔ ያገኙ መሆኑን እንዲሁም 1,830 መዝገቦች ደግሞ በነጻ እንዲሰናበቱ ውሳኔ መሰጠቱ ተገልጿል፡፡

የመንግሥትና የሕዝብን ፍትሐብሔራዊ ጥቅም ከማስጠበቅ አንፃር በገንዘብ ሲተመን ከ23 ቢሊየን ብር በላይ እና 14 ሚሊዮን 6 መቶ ሺህ የአሜሪካን ዶላር በላይ ክርክር መደረጉን፣ በግማሽ ዓመቱ 58 ሺህ 4 መቶ 78 በማረሚያ ቤት እና በፖሊስ ማረፊያ ቤት ውስጥ የሚገኙ ታራሚዎች መጎብኘታቸውን እንዲሁም ለ6 ሺህ 13 ዜጎች ነፃ የሕግ አገልግሎት የተሰጠ መሆኑን ሪፖርቱ ያመለክታል፡፡

ምርመራቸው ተጠናቆ የሚቀርቡ መዝገቦችን (በፍትሕ ሚኒስቴር 27,168 እና በክልሎች ፍትሕ ቢሮ 69,007) በአጠቃላይ እንደ አገር 98,348 የምርመራ መዝገቦች በዐቃቢያነ ሕግ እጅ የነበሩ ሲሆን 93,991 መዝገቦች ላይ ዐቃቤ ሕግ የተለያዩ ውሳኔዎችን የሰጠ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

ከሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አንጻር የሽግግር ፍትሕ ሀገራዊ ፖሊሲ ይዘት ግብዓት ሊሆኑ በሚችሉበት አግባብ በመሰነድ እና በፖሊሲ አማራጮቹ ላይ የተገኙ ዋና ዋና ግኝቶችን ፣ ማጠቃለያዎችን እና ምክረ ሃሳቦችን የያዘ ዝርዝር ሪፖርት ለሕዝብ ይፋ መደረጉም በሪፖርቱ ተካቷል፡፡

ቀጥሎም የኢትዮጵያ የፍትሕ አካላት የ3 ዓመት ትራንስፎርሜሽን እቅድ የ6 ወራት አፈፃፀም ሪፖርት የተቋም ግንባታ እና ሪፎርም ዘርፍ አማካሪ አቶ አማኑኤል ታደሰ በዝርዝር አቅርበዋል፡፡

ይህንንም ተከትሎ በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ በመድረኩ ተሳታፊዎች ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎችና ለተሰጡ አስተያቶች በፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ እና በፍትሕ ሚኒስቴር የሶስቱም ዘርፎች ሚኒስትር ዴኤታዎች መድረኩ እየተመራ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ለቀጣይ 6 ወራትም የትኩረት አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል፡፡

በመጨረሻም የቀድሞ የፍትሕ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ለነበሩት አቶ አለምአንተ አግደው እና አቶ ፍቃዱ ፀጋ የምስጋና እና የሽኝት መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡

Tagged Under: aid • alemante agdew • Budget • budget performance review • case • case files • court • court decisions • Criminal Justice • decisions • dr. gideon timotheos • fikadu tsegaye • files • judicial reform • Justice Sector Reform • legal • Legal Aid • national policy • performance • prison • prison visits • report • review • Sentencing • six-month • six-month report • strategic issues directorate • transformation plan • Transitional Justice Policy
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች