የሪፎርምና ተቋም ግንባታ ሚንስትር ዴኤታ

ኤርሚያስ የማነብርሃን ኃይለማርያም (ዶ/ር)

የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ


ኤርምያስ የማነብርሃን (ዶ/ር)፣ከሚያዝያ 2015 ዓ.ም ጀምሮ፣ የፍትህ ሚኒስቴር፣ የተቋም ግንባታ እና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው፣ በማገልገል ላይ ይገኛሉ። ከ2003-2007፣ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የህግ ሌክቸረር የነበሩ ሲሆን፣ በህገ መንግስት ትርጉም፣ በሰባዊ መብት ፣ በፌዴራሊዝም፣ በበፌዴራል ስርአቶች የልማት አስተዳደር እና በሌሎችም ርዕሶች ላይ፣ ፅሁፎችን አሳትመዋል፡፡ ከ2008-2015፣ የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣንን በዋና ዳይሬክተር ያገለገሉ ሲሆን፣ በዚህም ወቅት፣ የሀገራችን የአዕምሯዊ ንብረት ህጎች፣ ከአለም አቀፉ ደረጃዎች ጋር የማጣጣም ሪፎርሞችን መርተዋል፡፡ አዕምሯዊ ንብረት ለፈጠራ፣ ለቴክኖሎጂ ሽግግር እና ለኢንቨስትመንት መሳሪያ ሆኖ እንዲያገለግል ጥረዋል፡፡ ኤርምያስ የማነብርሃን (ዶ/ር)፣ በፌዴራል ማናቸውም ፍርድ ቤት በጠበቃነትም ሰርተዋል፡፡ የፍትህ ዘርፍ ሪፎርምን በአቅም ግንባታ እና በዲጂታላይዜሽን እንዲታደዝ ከማድረግ በተጨማሪ፣ የማህበረሰብ ፍትሕ አገልግሎትን በማስፋፋት፣ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት፣ ሀገር አቀፍ የፍትህ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ፍኖተ ካርታን (2016-2018) ያስተባብራሉ።

የትምህርት ዳራ

  • ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ፣ በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ
  • አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ በፌዴራሊዝምና አስተዳደር ጥናት ሁለተኛ ዲግሪ
  • አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ በፌዴራሊዝምና አስተዳደር ፒኤችዲ ዲግሪ

የሥራ ክፍሉን ያግኙ

News From State Minister for Reform and Institutional Building Division