የፍትሕ ሚኒስቴር የባህል ፍርድ ቤቶች ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ

Ministry of Justice Pledges Continued Support to Ensure Accessibility of Customary Courts

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ከUnited Nations Development Programme እና Hague Institute for Innovation of Law ጋር በመተባበር ለደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሺሺንዳ ሞዴል ባህላዊ ፍርድ ቤት የቢሮ ዕቃዎች እና ለሽማግሌዎች የአቅም ግንባታ የሥልጠና የወጪ ድጋፍ አደረገ።

የሞዴል የባህል ፍርድ ቤቱ ይፋዊ የሥራ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር የፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኤርምያስ የማነብርሃንን ጨምሮ የሺሺንዳ ከተማ ከንቲባ፤ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት፤ የክልሉ ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም የማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽነር በተገኙበት ሰኔ 4/2018 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡

በመርሃ-ግብሩ ወቅት እንደተገለፀው በክልሉ 700 ቀበሌዎች ላይ ባህላዊ ፍርድ ቤቶች የተቋቋሙ ሲሆን፤ በበጀት ዓመቱ ብቻ 1‚700 በላይ መዛግብቶችን መታየት ችለዋል፡፡

የፍትሕ ሚኒስቴርም በክልሉ የባህል ፍርድ ቤቶች ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እና የተቋቋሙትን አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚደረገውን እንቅስቃሴ ከአጋር አካላቶቹ ጋር በመሆን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳታውቋል፡፡

በነገው እለትም የድጋፉ አካል የሆነው የባህል ፍርድ ቤት ሽማግሌዎች የአቅም ግንባታ ሥልጠና መርሃ-ግብር እንደሚጀምር ተጠቁሟል፡፡

Tagged Under: access • accessibility • act • court • Courts • customary • decree • development • development program • hague • innovation • institute • itu • judiciary • Justice • law • legislation • ministry • Nations • port • pro • proclamation • program • programme • statute • support • United nations
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች
በብሔራዊና ክልላዊ የትብብር ጥምረቶች የሕግ ማስከበር የሥራ ቡድን ዓመታዊ የትብብር ሥራዎች ሀገራዊ አፈጻጸም እና የክስና ምርመራ ሥራዎችን ለማሻሻል የተዘጋጀው የአሠራር ሥርዓት ሰነድ ትግበራን በተመለከተ የግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል•A review forum is underway to assess the implementation of the operational framework document developed to improve the national implementation of annual joint activities of the Law Enforcement Working Group under national and regional partnership coalition, as well as to enhance prosecution and investigation activities
በጀርመን መንግስት ድጋፍ በፍትሕ ሚኒስቴር ተዘጋጅተው የታተሙት የሰብዓዊ መብቶች አገራዊ የአፈጻጸም ሪፖርት ዝግጅትና አቀራረብ እንዲሁም የሰብዓዊ መብቶች ክትትል ማብራሪያ መጽሐፍት ርክክብ ተደረገ•A handover ceremony was held for the National Human Rights Implementation Reporting, Preparation and Presentation Manual and the Human Rights Monitoring Guidebooks, prepared and published by the Ministry of Justice with the support of the German Government

ተመሳሳይ ዜናዎች