በኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ መንግስታት መካከል ፍርደኞችን ለማስተላለፍ የሚያስችል የሁለትዮሽ ስምምነት አደረጉ

Ethiopia and Nigeria Sign Bilateral Agreement on Prisoners Transfer

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በናይጄሪያ ፌዴሬሽን መካከል ፍርደኞችን ለማስተላለፍ የሚያስችል የሁለትዮሽ ስምምነት የፊርማ ሥነ ሥርዓት ሰኔ 03 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተከናውኗል።

በኢትዮጵያ በኩል ስምምነቱን የፈረሙት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፍትሕ ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሐና አርዓያስላሴ ሲሆኑ በናይጄሪያ በኩል የሀገሪቷ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና የፍትሕ ሚኒስትር ክቡር ሚ/ር Lateef Olasunkanmi Fagbemi ናቸው።

በፈርማ ሥነ ሥርዓቱ የሁለቱ አገራት ግንኙነት ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ መሆኑ የተነሳ ሲሆን አገራቱ በተለያዩ ዘርፎች በትብብር በመስራት ላይ ስለመሆናቸው ተጠቅሷል። በፍትሕ ዘርፍ ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር የተፈረመው ስምምነት ትልቅ መነሻ እንደሚሆን እንዲሁም በዕለቱ ከተፈረመው የፍርደኞች ማስተላለፍ ስምምነት በተጨማሪ በሌሎች የሕግ ጉዳዮች በትብብር ለመስራት ሁለቱ አገራት ዝግጁነታቸውን ገልፀዋል።

ስምምነቱ በአግባቡ እንዲፈጸም ትኩረት መስጠት እንደሚገባ በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተጠቆመ ሲሆን በዚሁ ወቅት የሁለቱም አገራት የፍትሕ ሚኒስትሮች ስምምነቱን ተፈጻሚ ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኝነት እና ዝግጁነት ገልጸዋል።

Tagged Under: 1994 agreement 1996 agreement 1997 agreement 1998 agreement 1999 agreement 2000 agreement agreement and healthcare administration and control authority bilateral Bilateral Agreement bilateral air services agreement bilateral tax agreement bilateral trade agreement ethiopia revenue and customs authority justice for all prison fellowship ethiopia medicine and healthcare administration and control authority medicine and healthcare administration and control proclamation no. 661/2009 nigeria one prison prisoner Prisoner Transfer prisoner transfer treaty prisoners technical and vocational education and training technical and vocational education and training (tvet) transfer un
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች