የፍትሕ ዘርፉን ስትራቴጂ መሠረት ያደረገ የዕቅድ፣ ፕሮጀክትና በጀት ዝግጅት፣ ክትትል እና ግምገማ የማድረግና የፖሊሲ እና ፕሮግራም ሥራዎችን የመከታተል እና የማስፋት ሥራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ የተቋሙን ስትራቴጂክና ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ የዕቅድ አፈፃፀም ክትትልና ድጋፍ ሥርዓት ይዘረጋል፣ ስትራተጅያዊ እይታ አማላካች ግቦችና ቀርጾ እንዲተገበር ያደርጋል፣ የአፈጻጸም መመዘኛ መስፈርቶችን በማዘጋጀት በሥራ ላይ ያውላል፣ የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶች ላይ ለሥራ ክፍሎች ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የተቋሙን ፕሮግራም በጀት በማዘጋጀት ሥራ ላይ መዋሉን ይከታተላል።
የፕሮጀክቶች ዝግጅትና አፈጻጸም ክትትል ሥራዎችን ይሰራል። የፕሮጀክት አፈፃፀም ክንውን ሪፖርት ወቅቱን ጠብቆ መቅረቡን ያረጋግጣል፤ ይገመግማል፤ የተጠቃለለ ሪፖርት አዘጋጅቶ ያቀርባል። የግንባታ ፕሮጀክቶችን የተመለከቱ ክፍያዎች ወቅቱን ጠብቀው የተጠየቁ መሆናቸውን እና ሥራዎች በትክክል መሰራታቸውን አረጋግጦ ለውሣኔ ለሚመለከተው ያቀርባል ሲወሰንም አፈፃፀሙን መከታተል ከተጣሉበት ኃላፊነቶቹ መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
