የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የ2017 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸምን በትላንትናው ዕለት ግምገማ አካሂዷል፡፡
ግምገማው የተካሄደው የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ተስፋዬ ዳባን ጨምሮ የዘርፉ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ በረከት ማሞ እንዲሁም የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌቱ ታደሰ በቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ በተገኙበት ነበር፡፡
የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቃሲም አማን የ2017 ዓ/ም የጽህፈት ቤቱን የስድስት ወራትን ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን፣ በሪፖርቱ በበጀት ዓመቱ በዕቅድ የተያዙ ዋና ዋና ግቦች አፈጻጸም፣ በዕቅድ አፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ችግሮች፣ የተለዩ ጥንካሬዎች እና ውስንነቶች ተነስተው ከፅ/ቤቱ ሰራተኞች ጋር ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
ክቡር አቶ ተስፋዬ ዳባ በበኩላቸው በቀረበው ሪፖርት ላይ አበረታች ውጤት መመዝገቡን በማንሳት ዐቃብያነ ሕግ ስራቸውን በላቀ ስነ-ምግባር ማከናወን እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በሪፖርቱም ላይ የምርመራ እና የክርክር መዛግብት አፈፃፀም፣ የምስክሮችና ተከሳሾች አቀራረብ እና ተያይዥ ጉዳዮች ተነስተው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን አፈፃፀሙ እየተሻሻለ መምጣቱን እና በቀጣይ መስተካከል ያሉባቸውን ጉዳዮች በመለየት ትኩረት በመስጠት እንዲሰራ አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን ፣ ድሬደዋ ከሚገኙት ባለድርሻ አካላት ጋር በሚቀጥሉት ቀናት ዉይይቱ እንደሚቀጥል በመድረኩ ተመላክቷል፡፡