የፍትሕ ሚኒስቴር የህብረተሰቡን ንቃተ ህግ ለማሳደ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነ ተመላከተ

Ministry of Justice Focuses on Enhancing Public Legal Awareness

የፍትሕ ሚኒስቴር ንቃተ ሕግ፣ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት ከኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አቀፍ ሬዲዮ ማህበር እና ከፍትሕ ለሁሉም (Justice For All) ጋር በመተባበር ለማኅበረሰብ ሬዲዮ ጋዜጠኞች በሚዲያ የስርአተ-ጾታ አካቶ ትግበራ፣ ሚዲያ እና የሚዲያ ሕግና ዘገባ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሥልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡

በዚህም ወቅት በፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታ እና ሪፎርም ዘርፍ ተቋሙ በአዋጅ የተሰጠውን ኃላፊነት በመወጣት የሕግ የበላይነትን ለማስፈን በተለይም የህብረተሰቡን ንቃተ ሕግ ለማሳደግ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀው፣ የማኅበረሰብ አቀፍ የሬዲዮ ጋዜጠኞችን አቅም መገንባት የዚሁ ተግባር አንዱ እና ዋነኛው አካል መሆኑን ተናግረዋል።

አያይዘውም በሶስት አመቱ የሕግና ፍትሕ ትራንስፎርሜሽን እቅድ ከተካተቱ አምዶች መካከል የመሰረተ ማኅበረሰብ ፍትሕ አገልግሎትን ማሳደግ አንደኛው መሆኑን አስታውሰው፣ ለዚህ ተግባር መሳካትም ለማህበረሰቡ ተደራሽ የሆኑትን የማኅበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች ሕግን ለማስገንዘብ ብሎም ሕዝብን መሠረት ያደረገ ምላሽ ለመስጠት ያላቸው ሚና የጎላ መሆኑን ገልፀዋል።

በመሆኑም ፍትሕንና የሕግ የበላይነትን አስመልክቶ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ንቃተ ሕግን ለመፍጠርና መረጃውን ተደራሽ ለማድረግ ከኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ሬዲዮ ማህበር ጋር አብሮ ለመሥራት የሚያስችል ስምምነት መፈረሙን ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አውስተው፣ ሕግ አክባሪ፣ መብቱን የሚያውቅና ግዴታውን የሚወጣ የነቃ ማኅበረሰብ በመፍጠር በኩል የድርሻቸውን እንዲወጡ አደራ ብለዋል።

የፍትሕ ለሁሉም (Justice For All) የፌደራሊዝምና የዲሞክራሲ ሲኒየር አማካሪ ዶ/ር ዘሪሁን ይመር በበኩላቸው ድርጅታቸው ባለፉት አመታት በተለያዩ ጊዚያት የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን በመስጠት በኩል ከፍትሕ ሚኒስቴር ጋር በጋራ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውሰው፣ በዛሬው እለት ከህብረተሰቡ ጋር በቀጥታ ለሚገናኙና ቅርብ ለሆኑ የማኅበረሰብ ሬዲዮ ጋዜጠኞች እየተሰጠ ያለው ሥልጠና የሕግ የበላይነትንና መልካም አስተዳደርን በማስፈን በኩል የሚኖረው ጠቀሜታ የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

በሥልጠናው ከመላው አገሪቱ የተውጣጡ የማኅበረሰብ ሬዲዮ የስራ ሀላፊዎች እና ጋዜጠኞች እየተሳተፉ ሲሆን፣ በሁለት ቀናት ቆይታው በሕግ ጉዳዮች የሚዲያ አዘጋገብ፣ ስርአተ ጾታን በሚዲያ አካቶ መሥራት እና የሚዲያ ሕግ የሚዳሰሱበት ይሆናል።

የቅርብ ጊዜ ዜናዎች