በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሀና አርአያስላሴ የተመራ ልኡክ ቦንጋ ሚዛን አማን ከተማ በመገኘት የፍትህ ትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈፃፀም ገመገመ

Justice Minister-Led Delegation Reviews Justice Transformation Plan in Southwest Ethiopia

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሀና አርአያስላሴ የተመራ እና የፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኤርሚያስ የማነብርሃንን ያካተተ የሀገራዊ የፍትሕ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን የድጋፍና ክትትል ቡድን በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት የሁለት ዓመት የትራንስፎርሜሽን አፈፃፀም ያለበትን ደረጃ ለመገምገም ቦንጋ እና ሚዛን አማን ከተማ ተገኝተዋል፡፡

የልኡካን ቡድኑ ወደ ክልሉ ሲገባ የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መስተዳደር ክቡር ዶ/ር ነጋሽ ዋጌሾ እና የክልሉ የፍትሕ ዘርፍ አመራሮች አቀባበል ያደረጉላቸዉ ሲሆን በመቀጠል የፍትሕ ቢሮ ሀላፊ፣ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር፣ የክልሉ ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽነር እና ሌሎችም የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት በክልሉ የፍትሕ ትራንስፎርሜሽን እቅድ የሁለት አመታት አፈጻፀም ሐምሌ 02 እና 03 ቀን 2017 ዓ/ም በጥልቀት ገምግሟል።

ክብርት የፍትሕ ሚኒስትር ወ/ሮ ሀና አርአያስላሴ ክልሉ ላደረገው አቀባበል አመስግነው የመድረኩ ዓላማ በሀገር ደረጃ የታቀደው የሶስት ዓመት የፍትሕ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ትግበራ የደረሰበትን ደረጃ ለማየትና አስፈላጊውን ቅንጅትና ትብብር ለማድረግ ብሎም አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ለማድረግ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ክቡር ዶ/ር ኤርሚያስ የማነብርሃን በበኩላቸው የፍትሕ ሚኒስቴር ሀገር አቀፍ የፍትሕ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን እቅድን ለመተግበር ከክልሎች ጋር በትብብርና በቅንጅት እንደሚሰራ እና ተከታታይነት ባለው መልኩ የክልሎችን አፈፃፀም በመገምገም ጠንካራ ድጋፍና ክትትል የማድረግ አካል መሆኑን አንስተዋል፡፡ በመቀጠልም የክልሉ የሁለት አመታት የፍትሕ ዘርፍ የትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፤ ከትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ አስር አምዶች አኳያ የተከናወኑ ተግባራት በዝርዝር ቀርበዋል፡፡

በተለይም በማኅበረሰብ አቀፍ ፍትሕ አገልግሎት አምድ ስር ክልሉ የባህላዊ ዳኝነት አዋጅ አውጥቶ በመተግበር ላይ መሆኑ፣ የአስተዳደር ስነ ሥርዓት አዋጅ በክልሉ ወጥቶ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑ፣ በወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ውዝፍ መዝገቦች የማጥራት ስራዎች መከናወናቸው፣ የተቋረጡ መዝገቦችን መልሶ ለማንቀሳቀስ ስራዎች መሰራታቸው፣ የይቅርታ አሰጣጥ መመሪያ መሻሻሉ፣ የሚጣሉ የገንዘብ ቅጣቶች ገቢ ለማድረግ ስራዎች መሰራታቸው ተገልጿል፡፡

በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ማሳደግ አምድ ስርም ከሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ፍኖተ ካርታ በመዘጋጀት ላይ መሆኑ፣ የንቃተ ሕግ በክልሉ በሚገኙ ሚድያዎች እየተሰጠ መሆኑና ነፃ የሕግ ድጋፍ በዐቃቤያን ሕግና በዩኒቨርስቲዎች አማካኝነት እየተሰጠ መሆኑ፣ የተከላካይ ጠበቃ ጽ/ቤት ለማደራጀት ረቂቅ ሕግ መዘጋጀቱ፣ የፍትሕ አካላት ተደራሽነትን ለማስፋት እንዲሁም የህብረተሰብ ተሳትፎን ለማረጋገጥ የተሰሩ ስራዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

ክብርት ሚኒስትር ክልሉ የተሻለ እና ጠንካራ አፈፃፀም ማስመዝገቡን አንስተው በማኅበረሰብ ፍትሕ አምድ ስር የተከናወኑ ስራዎች ለሌሎች ክልሎች አርአያ ሊሆኑ እንደሚችሉ እና በአተገባበሩም ወቅት ሰብዓዊ መብትን የተከተለ መሆኑን፣ የሴቶችና ሕፃናትን መብት የሚያከብር መሆኑን ማረጋገጥ እንደሚገባ፣ የተጀመረው የቅንጅት አሠራርም በፌዴራል ካለው ተሞክሮ በመውሰድ ሥርዓት ተበጅቶለት እንዲመራ፣ በቀሪ ጊዜ ውስጥ ያልተጠናቀቁ ስራዎችን በትኩረት ለመፈፀም ጥረት ሊደረግ እንደሚገባ በመጠቆም የፍትሕ ሚኒስቴርም የተቻለውን አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

ይህን ተከትሎም በክልሉ የተሰሩ የልማት ስራዎችን፣ ተግባራዊ የተደረገውን የማኅበረሰብ ፍትሕ ባህላዊ ዳኝነት በሽሽንዳ ወረዳ የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት ምልከታ የተደረገ ሲሆን በመቀጠልም የክልሉ ማረሚያ ቤት እና የፍትሕ ቢሮ በመገኘት የመስክ ጉብኝት እና የአረንጓዴ አሻራም የችግኝ ተከላ ተከናውኗል፡፡

በመጨረሻም የተጀመረውን የክልሉን የትራንስፎርሜሽን እቅድ ትግበራ ለመደገፍ በፍትሕ ሚኒስቴር ደረጃ የተዘጋጁ የታክስና ጉምሩክ ወንጀሎች እንዲሁም በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ምርመራ፣ ክስ እና የችሎት ማስገንዘቢያ መጽሐፍት (Handbook) ለክልሉ ፍትሕ ቢሮ አስረክበዋል።

የፍትሕ ሚኒስቴርን የማኅበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

Tagged Under: 2017 agreement 2017 budget 2017 budget year 2017 proclamation 2017 ratification adama science and technology university Addis Ababa Science and Technology University addis ababa water and sewerage authority african charter on human and peoples’ rights african charter on the rights and welfare of the child african commission on human and peoples' rights and cultural rights and healthcare administration and healthcare administration and control authority and medium enterprises (msmes) and peoples' region and peoples' region (snnpr) arra (agency for refugees and returnees affairs) article 55(1) and (11) article 55(1) and (12) arts and culture budget year 2017 Business and Human Rights handbook medicine and healthcare administration and control authority medicine and healthcare administration and control proclamation no. 661/2009 technical and vocational education and training technical and vocational education and training (tvet)
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች